am_tn/num/04/05.md

1.3 KiB

ሠፈሩ ዝግጅት በሚያደርግበት ወቅት

እዚህ ላይ “ሠፈር”የሚለው ቃል የሚያመለክተው በሠፈሩ ውስጥ የሚገኙትን ሰዎች ነው፡፡“ሰዎቹ ዝግጅት በሚያደርጉበት ወቅት” (ከዋናው ሃሣብ ጋር የተያያዙ ነገሮችን ለመግለፅ የሚውል ቃል የሚለውን ይመልከቱ)

ከሠፈሩ በተነሱ ጊዜ

ይሄ የሚያመለክተው ሰዎች ወደ ሌላ ሥፍራ መጓዛቸውን ነው፡፡“ወደ ሌላ ሥፍራ መጓዝ” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

የምሥክሩንም ታቦት በእርሱ ይጠቅሉለበት

“እርሱ”የሚለው ቃል የሚያመለክተው ቅድስተ ቅዱሳኑን ከቅዱስ ቦታ የሚለየውን ነው፡፡

መሎጊያዎችን ያግቡ

የመገናኛ ድንኳኑን እንዲሸከሙ ለማስቻል መሎጊያዎቹ ከመገናኛው ድንኳኑ ጎን በቀለበት ውስጥ እንዲገቡ ይደረጋል፡፡ይሄ የበለጠ ሊብራራ ይችላል፡፡“መሎጊያዎቹን ከመገናኛ ድንኳኑ ጎን በሚገኙት ቀለበት ውስጥ አስገባቸው” (በግምት ላይ የተመሠረተ ዕውቀትና የተሟላ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)