am_tn/num/03/46.md

3.6 KiB

ለመዋጀት ሲባል

“መዋጀት”የሚለው ስም(ሰዋሰው) “መዋጀት”በሚለው ግሥ ሊተረጎም ይችላል፡፡“መዋጀት”(አሕፅሮተ ሥምን የሚለውን ይመልከቱ)

273 የበኩር ልጆች

“ሁለት መቶ ሰባ ሶስት የበኩር ልጆች”(ቁጥሮች የሚለውን ይመልከቱ)

የእሥራኤል የበኩር ልጆች

“የእሥራኤል ወንድ የበኩር ልጆች”

አምስት ሰቅል

አንድ ሰቅል በግምት ከ11 ግራም ጋር የሚሰተካከል ነው፡፡“55 ግራም አካባቢ”(የመፅሐፍ ቅዱስ ሚዛንና የመፅሐፍ ቅዱስ ገንዘብ የሚለውን ይመልከቱ)

የሌዋውያንን ቁጥር የሚበልጡትን

ይሄ ማለት ከአጠቃላይ የሌዋውያን ቁጥር ይልቅ በእሥራኤል ውስጥ በሚገኙ ለሎች ነገዶች ውስጥ 273 ወንዶች አሉ ማለት ነው፡፡

እንደ መቅደሱ ሰቅል ሚዛን ትወስዳለህ

ይሄ ማለት የሰቅሉ ሚዛን ቤተመቅደስ ውስጥ ከሚገኙት ጋር ተመሳሳይነት ሊኖረው ይገባል ማለት ነው፡፡“ለሰቅሉ ሚዛን መለኪያ የምታደርገው ቤተመቅደሱ ውስጥ ካለው ጋር በማስተያየት ነው”(በግምት ላይ የተመሠረተ ዕውቀትና የተሟላ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

ሃያ አቦሊ

“ሃያ አቦሊ”አንድ አቦሊ ከ .57 ኪሎ ግራም ጋር ተመጣጣኝነት ያለው ነው፡፡(ቁጥሮች የሚለውንና መፅሐፍ ቅዱሣዊ ሚዛን የሚለውን ይመልከቱ)

የመቤዣውን ገንዘብ የከፈልከው

እዚህ ላይ“ገንዘብ”የሚለው ቃል የሚያመለክተው ሙሴ የሰበሰባቸውን ሰቅሎች ነው፡፡“ለመቤዣቸው የሰበሰብከው ገንዘብ” (ከዋናው ሃሣብ ጋር የተያያዙ ነገሮችን ለመግለፅ የሚውል ቃል የሚለውን ይመልከቱ)

ከ..የሚቤዡትን

ይሄ “መቤዠት”የሚለው ስም(ሰዋሰው) “ተቤዠ”በሚል ሥም ሊተረጎም ይችላል፡፡“መቤዠት”(አሕፅሮተ ሥምን የሚለውን ይመልከቱ)

1,365 ሰቅሎች

“አንድ ሺህ ሶስት መቶ ስድሣ አምስት ሰቅሎች”አንድ ሰቅል 11 ግራም አካባቢ ነው፡፡“ከላይ የተጠቀሱት የሰቅሎች ሚዛን 15 ኪሎ ግራም ብር አካባቢ ይሆናል”(ቁጥሮች የሚለውንና መፅሐፍ ቅዱሳዊ ገንዘብ የሚለውን ይመልከቱ)

የመቤዣ ገንዘብ

ይሄ የሚያመለክተው ሙሴ የሰበሰበውን ገንዘብ ነው፡፡

ለእርሱ ልጆች

እዚህ ላይ “የእርሱ”የሚለው ቃል የሚያመለክተው አሮንን ነው፡፡

በእግዚአብሔርን ቃል መሠረት ተግባራዊ እንዲያደርግ ተነገረው፤እግዚአብሔር እንዳዘዘው

በመሠረቱ እነዚህ ሁለት ሐረጎች ተመሳሳይ ትርጉም ያላቸው ሲሆን ተቀናጅተው የተነገሩትም ለጉዳዩ አፅንኦት ለመስጠት ሲባል ነው፡፡(ተመሳሳይነት የሚለውን ይመልከቱ)

በእግዚአብሔርን ቃል መሠረት ተግባራዊ እንዲያደርግ ተነገረው

እዚህ ላይ “የእግዚአብሔር ቃል” የሚለው ቃል የሚያመለክተው ለሙሴ የተናገረውን እግዚአብሔርን ነው፡፡(ገቢራዊና ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)