am_tn/num/01/53.md

1.2 KiB

የማደሪያው ድንኳን የሕግ ምሥክር

ማደሪያው በዚህ ረዥም ሥም የተጠራበት ምክኒያት የእግዚአብሔር ሕግ ያለበት ምሥክሩ በውስጡ በመቀመጡ ነው፡፡ይሄንን በኦሪት ዘኁልቁ 1፡50 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡

በእሥራኤል ልጆች ላይ ቁጣዬ እንዳይወርድ

እዚህ ላይ ቁጣው በእነርሱ ላይ ስለማይወርድ እሥራኤላውያንን እንደማይቀጣቸው ነው የሚናገረው፡፡“መውረድ”የሚለው ቃል የሚያመለክተው ቁጣው በእነርሱ ላይ ተግባራዊ የመሆኑን ጉዳይ ነው፡፡ “በቁጣዬ የእሥራኤልን ሕዝብ እንዳልቀጣ” (ምሣሌያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

እግዚአብሔር በሙሴ በኩል ትዕዛዝ አስተላለፈ

እግዚአብሔር እሥራኤላውያን ሊያደርጉት ስለሚገባቸው ነገር ለሙሴ የተናገረ ሲሆን ሙሴ ደግሞ ለእሥራኤላውያን ትዕዛዙን አስተላለፈ፡(በግምት ላይ የተመሠረተ ዕውቀትና የተሟላ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)