am_tn/num/01/50.md

1.1 KiB

የማደሪያው ድንኳን የሕግ ምሥክር

የማደሪያው ድንኳን በዚህ ረዥም ሥም የሚጠራበት ምከኒያት እግዚአብሔር የምሥክሩን ሕግ ያስቀመጠው እዚያ ውስጥ በመሆኑ ነው፡፡

በእርሱ ውስጥ ያለውን ሁሉ

“በእርሱ”የሚለው ቃል የሚያመለክተው የመገናኛ ድንኳኑን ነው፡፡

ሌዋውያን ማደሪያውን መሸከም ይኖርባቸዋል

ጉዞ በሚጀምሩበት ወቅት ማደሪውን የመሸከም ኃላፊነት የእነርሱ ነበር፡፡ “በምትጓዙበት ወቅት ሌዋውያን ማደሪያውን መሸከም ይኖርባቸዋል” (በግምት ላይ የተመሠረተ ዕውቀትና የተሟላ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

በማደሪያውም ዙሪያ ይስፈሩ

ይሄ ማለት ድንኳኖቻቸውን በማደሪያው ዙሪያ ይተክላሉ ማለት ነው፡፡“ድንኳኖቻቸውን በዙሪያው መትከል” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)