am_tn/neh/13/25.md

1.6 KiB

ተከራከርኳቸው

“ስለሰሩት ነገርም በቀጥታ ተናገርኳቸው”

አንዳንዶቹን መታኋቸው

ነህምያ አንዳንዶቹን በእጁ መታቸው፡፡

በእግዚአብሔር አስማልኳቸው

“በእግዚአብሔር ፊት ቃል አስገባኋቸው”

የእስራኤል ንጉስ ሰሎሞን በእነዚህ ሴቶች ምክንያት አልሳተምን?

ነህምያ ይህን መልስ የማይሰጥበት ጥያቄ ሰዎቹን ለመገሰጽ ተጠቀመ፡፡ ይህ በዓርፍተ ነገር ቅርጽ መጻፍ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “የእስራኤል ንጉስ ሰሎሞን በእነዚህ ሴቶች ምክንያት ኃጢአትን ማድረጉን ታውቃላችሁ” (መልስ የማይሰጥባቸው ጥያቄዎች የሚለውን ይመልከቱ)

ታዲያ እናንተን ሰምተን ይህንን ታላቅ ኃጢአት እናድርግ፣ እነዚህን እንግዳ ሴቶች በማግባትም አምላካችን ላይ በደል እናድርግ?

ነህምያ ሰዎቹን ለመገሰጽ ይህን መልስ የማይሰጥበት ጥያቄ ተጠቀመ፡፡ ይህ በዓርፍተ ነገር መልክ መጻፍ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እናንተን አንሰማም ወይም ይህን ታላቅ ኃጢአት አናደርግም ወይም እነዚህን እንግዳ ሴቶችም በማግባት አምላካችንን አንበድልም” (መልስ የማይሰጥባቸው ጥያቄዎች የሚለውን ይመልከቱ)