am_tn/neh/13/16.md

1.6 KiB

ጢሮስ

ይህ የአንድ ከተማ ስም ነው (ስሞችን እንዴት መተርጎም ይቻላል የሚለውን ይመልከቱ)

ይህ የምታደርጉት ክፉ ነገር ምንድን ነው፣ ሰንበትንስ ታረክሳላችሁን?

ነህምያ ይህን መልስ የማይሰጥበት ጥያቄ የይሁዳን አለቆች ለመገሰጽ ተጠመበት፡፡ ይህ በዓርፍተ ነገር መልክ መተርጎም ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “የሰንበትን ቀን በማርከስ ክፉ ስራን እየሰራችሁ ነው” ወይም “የሰንበትን ቀን በማርከስ ለሰራችሁት ክፉ ስራ እግዚአብሔር ይቀጣችኋል” (መልስ የማይሰጥባቸው ጥያቄዎች የሚለውን ይመልከቱ)

አባቶቻችሁ ይህን አድርገው አልነበረም? እግዚአብሔር በእኛና በከተማዋ ላይ ክፉ ነገርን ሁሉ አላመጣም?

ነህምያ እነዚህን መልስ የማይሰጥባቸውን ጥያቄዎች የይሁዳን አለቆች ለመገሰጽ ተጠቀመባቸው፡፡ እነዚህ ጥያቄዎች በአንድ ላይ በማያያዝና በመተርጎም በአንድ ዓረፍተ ነገር መጻፍ እንችላለን፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “አባቶቻችሁ ይህን እንዳደረጉ ታውቃላችሁ፣ እግዚአብሔር ይህን ሁሉ ክፉ ነገር በእኛና በዚህች ከተማ ላይ ያመጣው ለዚህ ነው” (መልስ የማይሰጥባቸው ጥያቄዎች የሚለውን ይመልከቱ)