am_tn/neh/11/17.md

1.3 KiB

መታንያ … ሚካ … ዘብዲ … አሳፍ … በቅበቃር … አበድያ … ሳሙስ … ጋላል … ኤዶታም

እነዚህ የወንድ ስሞች ናቸው፡፡ (ስሞችን እንዴት መተርጎም ይቻላል የሚለውን ይመልከቱ)

ምስጋናንም በጸሎት የሚጀምሩ

ይህ ማለት ዘማርያኑን የሚመሩ ነበሩ ማለት ነው፡፡

በወንድሞቹ መካከል ሁለተኛ የነበረ በቅበቃር

ለዚህ አማራጭ ትርጉም ሊሆኑ የሚችሉት 1) በቅበቃር የመታንያ ዘመድ የነበረና በስልጣን ከመታንያ ቀጥሎ ሁለተኛ ሰው ነበር ወይም 2) “ሌሎች ሁለተኛውን የመዘምራንን ቡድን ይመራ የነበረ በቅበቃር”

ወንድሞች

ሌላ አማራጭ ትርጉም የሚከተሉት ሊሆኑ ይችላ “ተባባሪዎች” እና “አብረው የሚሰሩ ሰራተኞች፡፡”

ቅድስቲቱ ከተማ

ይህ መግለጫ የሚወክለው የኢየሩሳሌምን ከተማ ነው፡፡

ቁጥራቸው 284 ነበር

“ቁጥራቸው ሁለት መቶ ሰማንያ አራት ነበር፡፡” በኢየሩሳሌም 284 ሌዋውያን ነበሩ፡፡ (ቁጥሮች የሚለውን ይመልከቱ)