am_tn/neh/09/28.md

1.8 KiB

አያያዥ ዓርፍተ ነገር፡-

በእነዚህ ቁጥሮች ሌዋውያን በእስራኤል ሕዝብ ፊት ያሕዌን ማመስገን ቀጠሉ፡፡

እነርሱ ባረፉ ጊዜ ደግመው በአንተ ፊት ክፉን አደረጉ

“እነርሱ” የሚለው ቃል የሚወክለው እስራኤላውንን ሲሆን “አንተ” የሚለው ደግሞ ያሕዌን ይወክላል፡፡

አንተ በጠላቶቻቸው እጅ ተውካቸው

እዚህ ላይ “እጅ” የሚለው ኃይል እና በቁጥጥር ስር ማድረግን ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “አንተ ተውኻቸው ጠላቶቻቸውም እንዲያሸንፏቸው አደረግህ” (ምትክ ስም የሚለውን ይመልከቱ)

ትዕዛዝህን አልሰሙም

“መስማት” ለሚለው ቃል “መታዘዝ” የሚል ተመሳሳይ ትርጉም ያለው ቃል በቋንቋችሁ ካለ እዚህ ላይ እሱን መጠቀም ትችላላችሁ፡፡

ለሚታዘዛቸው ለማንኛውም ሰው ሕይወትን የሚሰጡት ትዕዛዞችህ

እዚህ ክፍል ላይ ያሕዌ ራሱ እንደ ሕግጋቱና ትዕዛዛቱ ተደርጎ ነው የተነገረው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “አንተ ትዕዛዝህን ለሚጠብቁ ሁሉ ሕይወትን የምትሰጥ ነህ” (ምትክ ስም የሚለውን ይመልከቱ)

እምቢተኛ ሆነው ጀርባቸውን አዞሩብህ፤ አንገታቸውን አደነደኑ

እነዚህ መግለጫዎች አንድ በሬ ባለቤቱ በጫንቃው ላይ ቀንበር ሊያስረው ሲሞክር እምቢተኛ መሆኑን የሚያሳዩ ናቸው፡፡ እዚህ ላይ ያሉት ተለዋጭ ዘይቤዎች ሕዝቡ አንገተ ደንዳና እንደሆነ የሚያሳዩ ናቸው፡፡