am_tn/neh/09/26.md

1.4 KiB

አያያዥ ዓርፍተ ነገር፡-

በእነዚህ ቁጥሮች ሌዋውያን በእስራኤል ሕዝብ ፊት ያሕዌን ማመስገን ቀጠሉ፡፡

እነረሱ ሕግህን ከጀርባቸው ጣሉ

ሕጉ አንድ ሰው እንደሚጥለው እንደማይረባ ነገር ተደርጎ ተነግሯል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ሕግህን ጥቅም እንደሌለው አሰቡ ከዚህ የተነሳ ለሕጉ ትኩረት አልሰጡትም” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ሕግህን ጣሉ

እስራኤላውያን የያሕዌን ሕግ ጣሉ

ላሰቃዩአቸው ለጠላቶቻቸው እጅ አሳልፈህ ሰጠሃቸው

እዚህ ላይ “እጅ” የሚያመለክተው ኃይል እና በቁጥጥር ስር ማድረግን ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ጠላቶቻቸው እንዲያሸንፏቸውና እንዲያሰቃዩአቸው ፈቀድክ” (ምትክ ስም የሚለውን ይመልከቱ)

ከጠላቶቻቸው እጅ ያዳኗቸውን ታዳጊዎች ላክህላቸው

እዚህ ላይ “እጅ” የሚያመለክተው ኃይልና በቁጥጥር ስር ማድረግን ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ጠላቶቻቸው እንዳይጎዷቸው ሰዎችን ላክህላቸው” (ምትክ ስም የሚለውን ይመልከቱ)