am_tn/neh/09/16.md

1.8 KiB

አያያዥ ዓርፍተ ነገሮች፡-

በእነዚህ ቁጥሮች ሌዋውያን በእስራኤል ሕዝብ ፊት ያሕዌን ማመስገን ቀጠሉ፡፡

እነርሱና አባቶቻችን

በሙሴ ጊዜ የነበሩት እስራኤላውያን እና ከሙሴ ጊዜ በኋላ የነበሩት እስራኤላውያን

እነርሱ ግን ደንዳና ነበሩ … ደንዳና ሆኑ

ቀጥተኛ አባባሉ “አንገታቸውን አደነደኑ” የሚለው ነው፡፡ ቋንቋችሁ ደንዳና ስለመሆን የተለየ ፈሊጣዎ መግለጨ ካለው እርሱን መጠቀም ይቻላል፡፡ (ፈሊጥ የሚለውን ይመልከቱ)

በመካከላቸው ያደረግኸው ተዓምራት

“በመካከላቸው ያደረግኸው ድንቆች”

ወደ ባርነት ለመመለስ መሪ ሾሙ

እስራኤላውያን የቀደሙት አባቶቻቸው ወደ ግብጽ ለመመለስ መፈለጋቸውን ሊያውቁ እንደሚገባቸው ለማሳየት ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ባርያ ወደነበሩበት ወደ ግብጽ እንዲመልሳቸው መሪን ሾሙ” (ግምታዊ እውቀትና ያለተገለጸ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

በይቅርታ የተሞላ

ይቅርታን መፈለጉ የውሃ መያዣን እንደሚሞላ ፈሳሽ ተመስሎ ቀርቧል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ይቅር ለማለት ዝግጁ የሆነ” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ጽኑና የማያወላውል ፍቅር የተሞላ

እዚህ ላይ ፍቅር ያሕዌ ለሕዝቡ እንደሚያካፍለው እንደ ምግብ እህል ተደርጎ ቀርቧል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ሕዝቡን በጣም ይወድዳል” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)