am_tn/neh/09/01.md

1.2 KiB

በዚህም ወር በሃያ አራተኛው ቀን

“በሰባተኛው ወር በሃያ አራተኛው ቀን” ይህ በምዕራባውያን ቀን መቁጠርያ በጥቅምት ወር አጋማሽ አካባቢ ነው፡፡ (የዕብራይስጥ ወራት እና ደረጃ የሚያሳዩ ቁጥሮች የሚለውን ይመልከቱ)

የእስራኤል ልጆች ተከማቹ

“የእስራኤል ሕዝብ አንድ ላይ ተሰበሰቡ”

ማቅ ለብሰው፣ በራሳቸውም ላይ ትቢያን ነስንሰው

እንዲህ ያደረጉት እነርሱና አባቶቻቸው ላደረጉት ትክክል ያልሆነ ነገር ምን ያህል እንዳዘኑ ለማሳየት ነው፡፡ (ግምታዊ እውቀትና ያለተገለጸ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

የእስራኤል ዘር

“እስራኤላውያን”

ከእንግዶች ሁሉ ራሳቸውን ለዩ

“እስራኤላዊ ካልሆኑ ሰዎች ጋር ህብረታቸውን አቋረጡ”

ቆመው የራሳቸውን ኃጢአትና አባቶቻቸውንም የፈጸሙትን ክፉ ስራ ተናዘዙ

“ራሳቸውና የቀደሙ አባቶቻቸው የሰሯቸውን ክፉ ስራዎች ተናዘዙ”