am_tn/neh/08/09.md

1.4 KiB

ሕዝቡ ሁሉ ያለቅሱ ነበርና

ይህ በሕዝቡ ዘንድ ታላቅ ለቅሶ እንደነበር የሚያሳይ ጅምላ ገለጻ ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ሕዝቡ በጣም ያለቅስ ነበርና” (ግነትና ጅምላ መግለጫ የሚለውን ይመልከቱ)

የሰባውን ብሉ ጣፋጩንም ጠጡ

ይህ በተዛዋሪ የቀረበ መረጃ የሚያሳየው ሕዝቡ በጥሩ ምግብና መጠጥ እንዲያከብሩ እንደተነገራቸው የሚያሳይ ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ጥሩ የሆነ ምግብና ጣፋጭ መጠጥ ተመገቡ” (ግምታዊ እውቀትና ያልተገለጸ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

አትዘኑ

ይህ በገቢር/አድራጊ ቅርጽ መጻፍ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “አትዘኑ” (ገቢር/አድራጊ ወይም ተገብሮ/ተሳቢ የሚለውን ይመልከቱ)

የያሕዌ ደስታ ኃይላችሁ ነውና

እዚህ ላይ “ደስታ” እና “ኃይል” የሚሉት ረቂቅ ቃላት በግስና ገላጭ መልክ መቀመጥ ይችላሉ፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “በያሕዌ ሐሴት ማድረግ ይጠብቃችኋል” ወይም “በያሕዌ መደሰት ብርቱ መጠጊያ ይሆናችኋል” (ረቂቅ ስሞች የሚለውን ይመልከቱ)