am_tn/neh/08/04.md

1.1 KiB

መቲትያ … ሽማዕ … ዓናያ … ኦርዮ .. ኬልቅያስ … መዕሤያ … ፈዳያ … ሚሳኤል … መልክያ … ሐሱም … ሐሽበዳና … ዘካርያስ … ሜሱላም

እነዚህ ሁሉም የወንድ ስሞች ናቸው፡፡ (ስሞችን እንዴት መተርጎም ይቻላል የሚለውን ይመልከቱ)

ዕዝራ በሰዎች ሁሉ ፊት መጽሐፉን ከፈተ

“ፊት” የሚለው ረቂቅ ስም የሚናገረው “ተመለከቱ” በሚለው ግስ ሊተካ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ሁሉም ሰዎች ዕዝራ መጽሐፉን ሲከፍተው ተመለከቱት” (ረቂቅ ስሞች የሚለውን ይመልከቱ)

መጽሐፉ

“የሕጉ መጽሐፍ”

በሕዝቡ ላይ ከፍ ብሎ ቆሞ

“ከሰዎቹ ከፍ ብሎ ቆሞ ነበር”

በገለጠው ጊዜ ሕዝቡ ሁሉ ተነስቶ ቆመ

ሕዝቡ ለእግዚአብሔር ቃል ያለውን አክብሮት ለመግለጽ ተነስቶ ቆመ፡፡ (ግምታዊ እውቀትና ያለተገለጸ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)