am_tn/neh/07/01.md

2.3 KiB

ቅጥሩ ተሰርቶ ካለቀ በኋላ

ይህ በገቢር/አድራጊ ቅርጽ መጻፍ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ቅጥሩን ሰርተን ስንጨርስ” (ገቢር/አድራጊ ወይም ተገብሮ/ተሳቢ የሚለውን ይመልከቱ)

በሮቹን በቦታቸው አደረግሁ

ይህ በሌላ ሰው እርዳታ የተደረገ ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እኔና ሌሎቹ በሮቹን ሰቀልን” (ተዛምዶአዊ የሚለውን ይመልከቱ)

በር ጠባቂዎቹ ዘማሪዎቹና ለሌዋውያን ተሾሙ

ይህ በገቢር/አድራጊ ቅርጽ መጻፍ ይቻላል፡፡ የሚከተሉት አማራጭ ትርገጉሞች ሊሆኑ ይችላሉ፡- 1) ነህምያ ሾማቸው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “በር ጠባቂዎቹን ዘማሪዎቹንና ሌዋውያኖቹን ለስራቸው ሾምኳቸው፡፡ ወይም 2) ሌላ ሰው ሾማቸው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “በር ጠባቂዎቹን ዘማሪዎቹንና ሌዋውያንን ለስራቸው ሾሙአቸው፡፡” (ገቢር/አድራጊ ወይም ተገብሮ/ተሳቢ የሚለውን ይመልከቱ)

በር ጠባቂዎች

ወደ ከተማውና ወደ መቅደሱ የሚገባውን ሰው ለመቆጣጠርና ገዢው በወሰነው ምክንያት በትክክለኛው ጊዜ በሩን እንዲከፍቱና እንዲዘጉ የተወሱ ሰዎች በእያንዳንዱ በር ላይ ተመደቡ፡፡

ዘማሪዎች

አምልኮ ላይ፣ ጉዞ ላይና የተለያዩ ዝግጅቶች ላይ ሙዚቃና ዜማን በድምጻቸው በመፍጠር ዝግጅቱ ትኩረት እንዲሰጠው የሚያደርጉ ወይም የሚያደምቁ ሰዎች፡፡

አናኒ … ሐናንያ

እነዚህ የወንድ ስሞች ናቸው፡፡ (ስሞችን እንዴት መተርጎም ይቻላል የሚለውን ይመልከቱ)

ወንድሜን አናኒን … ሾምሁት

“ወንድሜ አናኒ አስተዳዳሪ እንዲሆን አዘዝኩት”

የቅጥሩን አለቃ

“ቅጥሩን ይቆጣጠር የነበረው”

ከብዙዎች ይልቅ እግዚአብሔርን ይፈራ ነበር

“ከሌሎች ብዙ ሰዎች የበለጠ እግዚአብሔርን ይፈራ ነበር”