am_tn/neh/05/18.md

1.5 KiB

በየቀኑም … ይዘጋጅ ነበር

ይህ በገቢር/አድራጊ ቅርጽ መጻፍ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “በየቀኑም ሰራተኞቼን … እንዲያዘጋጁ እነግራቸው ነበር” ወይም “በየቀኑ ለሰራተኞቼ … ከመዓዱ እንዲያስተናናዱን እነግራቸው ነበር” (ገቢር/አድራጊ ወይም ተገብሮ/ተሳቢ የሚለውን ይመልከቱ)

ስድስት የተመረጡ … አስር ቀናት

“6 የተመረጡ … 10 ቀናት” (ቁጥሮች የሚለውን ይመልከቱ)

ብዙ ወይን

“ለሁሉም ሰው የሚበቃ ወይን”

ቢሆንም ግን ለአለቃ የሚገባውን የምግብ አበል አልሻም ነበር

“ቢሆንም ግን ለአለቃ የሚሰጠውን የምግብ አበል ፈጽሞ አልጠየቅሁም”

አስበኝ

ይህ ፈሊጥ ነው፡፡ ይህ እግዚአብሔር እንዲያስበውና እንዲያስታውሰው የቀረበ ልመና ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “አስታውሰኝ” (ፈሊጥ የሚለውን ይመልከቱ)

ለመልካም

ይህ ፈሊጥ ነህምያ ለሕዝቡ ስላደረገው መልካም ነገር በሙሉ እግዚአብሔር ዋጋ እንዲሰጠው የሚለምንበት ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ዋጋዬን ስጠኝ” ወይም “መልካም ነገሮችን እንዲሆኑልኝ አድርግ” (ፈሊጥ የሚለውን ይመልከቱ)