am_tn/neh/05/16.md

1.7 KiB

እኔም ቀጠልኩኝ

“እኔ” የሚለው የሚያመለክተው ነህምያን ነው፡፡

አልገዛንም

“አልገዛንም” የሚለው ቃል ውስጥ የባለቤት አመልካቹ የሚወክለው ነህምያና ሰራተኞቹን ነው፡፡

ሰራተኞቼም ወደ ስራው ተሰበሰቡ

ይህ በገቢር/አድራጊ ቅርጽ መጻፍ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ሰራተኞቼን በሙሉ ወደዚያ ሰበሰብኳቸው” (ገቢር/አድራጊ ወይም ተገብሮ/ተሳቢ የሚለውን ይመልከቱ)

ለስራው

“ቅጥሩን ለመገንባት”

150 ሰዎች

“አንድ መቶ አምሳ ሰዎች” (ቁጥሮች የሚለውን ይመልከቱ)

በገበታዬ አይሁዶች ነበሩ … በዙሪያችን ከነበሩ ከአሕዛብ መካልም ነበሩ

ነህምያ ለእነዚህ ሰዎች በሙሉ ምግብ የማቅረብ ኃላፊነት ነበረበት፡፡ ይህ በግልጽ መቀመጥ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ከዚህ በተጨማሪ በየቀኑ ከገበታችን 150 ሰዎች ከአይሁድና ከሹማምንት የመመገብ ኃላፊነት ነበረብኝ፤ እንዲሁም በዙሪያችን ካሉ አሕዛብ ሃገሮች የመጡ እንግዶችን እንግብ ነበር” (ግምታዊ እውቀትና ያለተገለጸ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

ገበታዬ

ይህ የገዢውን ገበታ ያመለክታል፡፡ ይህም ለማህበረሰቡና በተለያዩ ሃሳቦች ዙሪያ ለመወያየትም የሚጠቅም ገበታ ነበር፡፡

ሹማምንት

የመንግስት መሪዎች