am_tn/neh/05/09.md

2.4 KiB

እኔ ደግሞ አልኩ

“እኔ” የሚለው ቃል የሚወክለው ነህምያን ነው፡፡

እናንተ እያደረጋችሁ ያላችሁት

“እናንተ” የሚለው ቃል የሚወክለው የአይሁድ አለቆችን ነው፡፡

ጠላቶቻችን የሆኑትን የአሕዛብን ስድብ ለመከላከል እግዚአብሔር አምላካችንን በመፍራት ልትመላለሱ አይገባም?

ይህ ነህምያ አለቆቹን ለመገሰጽ የተጠቀመበት መልስ የማይሰጥበት ጥያቄ ነው፡፡ በዓርፍተ ነገር መልክ መተርጎም ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ጠላቶቻችን አሕዛብ እንዳይሰድቡን እግዚአብሔርን በመፍራት መመላለስ አለባችሁ” (መልስ የማይሰጥባቸው ጥያቄዎች የሚለውን ይመልከቱ)

አምላካችን እግዚአብሔርን በመፍራት ተመላለሱ

ይህ ፈሊጥ ነው፡፡ እዚህ ላይ “ተመላለሱ” የሚያመለክተው ስለ ሰው ባሕርይ እና የአኗኗር ዘይቤ ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ሕይወታችሁን እግዚብሔርን በሚያከብር መንገድ ኑሩ” (ፈሊጥ የሚለውን ይመልከቱ)

የጠላቶቻችን የአህዛብ ስድብ

“ስድብ” የሚለው ቃል “ስላቅ” እና “ሹፈት” ማለት ነው፣ በግስ መልክም መጻፍ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ጠላቶቻችን ከሆኑት ከአህዛብ ስድብ” ወይም “የጠላቶቻችን የአህዛብ ስድብ” (ረቂቅ ስሞች የሚለውን ይመልከቱ)

ማበደር

ማዋስ ወይም ተመልሶ እንዲሰጠን በመጠበቅ ለአንድ ሰው አንድ ነገር መስጠት

ብድሮች

ይህ አንድ ሰው ካለበት ብድር እንዲወጣ ወይም ብድሩን እንዲከፍል ከሌላ ሰው የሚዋሰው ብር፣ ምግብ ወይም ቁሳቁስ ነው፡፡ ስለዚህም ተበዳሪው የአበዳሪው ባለእዳ ይሆናል ማለት ነው፡፡

ከመቶ እጅ

ተበዳሪው ወለድ የሚጠየቅበት የብድሩ መጠን የተወሰነ ክፍል ነው፡፡

ከእነርሱ ወሰዳችሁ

“አስከፈላችኋቸው” ወይም “እንዲከፍሉ አደረጋችኋቸው”