am_tn/neh/05/06.md

2.4 KiB

ጩኸታቸውን በሰማሁ ጊዜ

“ጩኸት” የሚለው ቃል በግስ መልክ መጻፍ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ሲጮኹ በሰማሁ ጊዜ” (ረቂቅ ስሞች የሚለውን ይመልከቱ)

እያንዳንዳችሁ ከወንድማችሁ ላይ ወለድ ትወስዳላቸሁ

አንድ አይሁዳዊ ለሌላ አይሁዳዊ በወለድ ማበደር እንደማይችል እያንዳንዱ አይሁዳዊ ሊያውቀው የሚገባ ነገር ነበር፡፡ የዚህ ትርጉም በግልጽ መቀመጥ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እያንዳንዳችሁ ከወንድሞቻችሁ ወለድ ትወስዳላችሁ፣ እርሱ ደግሞ በሕጉ መሰረት ትክክል አይደለም” (ግምታዊ እውቀትና ያለተገለጸ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

ትልቅ ጉባኤ ሰበሰብሁባቸው

ይህ ማለት ብዙ ቁጥር ያላቸው ሰዎችን ሰብስቦ እነዚህን ክሶች በእነርሱ ላይ አቀረበ ማለት ነው፡፡ የዚህ ትርጉም በግልጽ መቀመጥ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ትልቅ ጉባዔ ሰብስቤ በእነርሱ ላይ እነዚህን ክሶች ተናገርኩባቸው” ወይም “በጉባዔ ፊት ከሰስኳቸው” (ግምታዊ እውቀትና ያለተገለጸ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

እናንተ ግን የገዛ ወንድሞቻችሁንና እህቶቻችሁን ሸጣችሁ እነርሱ ደግመው ለእኛ እንዲሸጡልን አደረጋችሁ

ይህ ማለት እነርሱ የቤተሰብ አባሎቻቸውን ባርያ እንዲሆኑ ለሌሎች አይሁዶች እየሸጧቸው ነበር ማለት ነው፡፡ የዚህ ትርጉም በግልጽ ሊቀመጥ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “የራሳችሁን ሰዎች ወገኖቻችሁ ለሆኑት ለአይሁዳውያን ባርያ እንዲሆኑና መልሰውም ለእኛ እንዲሸጡልን ሸጣችኋቸው” (ግምታዊ እውቀትና ያለተገለጸ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

ለአሕዛብ የተሸጡትን

ይህ በገቢር/አድራጊ ቅርጽ መጻፍ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ባርያ እንዲሆኑ ሰዎች ለአሕዛብ የሸጧቸውን” (ገቢር/አድራጊ ወይም ተገብሮ/ተሳቢ የሚለውን ይመልከቱ)