am_tn/neh/05/04.md

2.5 KiB

አሁንም ስጋችንና ደማችን እንደወንድሞቻችን ስጋና ደም ነው፣ ልጆቻችንም እንደ ልጆቻቸው ናቸው

እዚህ ስፍራ አይሁዳውያኑ ከሌሎች አይሁዳውያን ጋር በዘር አንድ እንደሆኑና እንደሌሎቹ አይሁዳውያን እነርሱም እንደሚጠቅሙ ይናገራሉ፡፡ የዚህ ትርጉም በግልጽ መቀመጥ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “የኛ ቤተሰቦችም እንደሌሎች አይሁዳውያን ቤተሰቦች አይሁዳውያን ናቸው፣ የእነርሱ ልጆች ለእነርሱ እንደሚጠቅሙ ሁሉ የኛም ልጆች ለእኛ በጣም ጠቃሚ ናቸው” (ግምታዊ እውቀትና ያለተገለጸ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

ስጋና ደማችን

ይህ እነርሱ የቤተሰብ አባላትን የሚያመለክት ፈሊጥ ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ቤተሰባችን” (ፈሊጥ የሚለውን ይመልከቱ)

ከሴቶች ልጆቻችንም የተወሰኑት በባርነት እየኖሩ ያሉ አሉ

ይህ በገቢር/አድራጊ ቅርጽ መጻፍ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ከሴት ልጆቻችን ውስጥ አንዳንዶችን ለባርነት ሸጠናቸዋል” (ገቢር/አድራጊ ወይም ተገብሮ/ተሳቢ የሚለውን ይመልከቱ)

ነገር ግን ሌሎች የኛን እርሻና የወይን ማሳ ይዘዋልና እነሱን ማዳን ከአቅማችን በላይ ነበር

የሰዎቹ እርሻና የወይን ማሳ በማስያዣ ተይዞ የእነርሱ ሰላልነበረ ምርት አምርተውና ገንዘብን አግኝተው ቤተሰባቸውን መደገፍ አይችሉም ነበር፡፡ የዚህ ሙሉ ትርጉም በግልጽ መቀመጥ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ነገር ግን ይህንን ሁኔታ መቀየር አልቻልንም፣ ምክንያቱም ሕይወታችንን መምራት የምንችልበት እርሻችንና የወይን ማሳችን አሁን ሌሎች ሰዎች በንብረትነት ይዘውታል” (ግምታዊ እውቀትና ያለተገለጸ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

ከአቅማችን በላይ ነው

ይህ የሚያሳየው አንድን ነገር ለማድረግ ተገቢው ግብአት እንደሌላቸው ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እኛ ማድረግ አልቻልንም” (ፈሊጥ የሚለውን ይመልከቱ)