1.2 KiB
1.2 KiB
ከሁሉም አቅጣጫዎች
ይህ ብዙ አቅጣጫዎችን ይወክላል፡፡ “ሁሉም” የሚለው ቃል “ብዙ” ይወክላል የሚለውን የሚያጋንን ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ከብዙ አቅጣጫዎች” (ግነትና ጅምላ መግለጫየሚለውን ይመልከቱ)
አስር ጊዜ ነገሩን
እዚህ ላይ 10 ቁጥር “ብዙ” የሚለውን ቃል የሚወክል ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ብዙ ጊዜ ነገሩን” (ምትክ ስም የሚለውን ይመልከቱ)
በተከፈቱ ስፍራዎች
“ለአደጋ በተጋለጡ ቦታዎች”
እያንዳንዱን ቤተሰብ አቆምኳቸው
ይህ ከእያንዳንዱ ቤተሰብ የተመረጡ ብዙ ሰዎችን ያመለክታል፣ ምርጫው ሴቶችንና ሕጻናትን እንደማይጨምር ይገመታል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ከያንዳንዱ ቤተሰብ ሰዎችን አቆምኩ” (ተዛምዶአዊ የሚለውን ይመልከቱ)
ጌታን አስቡ
“አስቡ” የሚለው ቃል ማስታወስ ማለት ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ጌታን አስታውሱ” (ፈሊጥ የሚለውን ይመልከቱ)