am_tn/neh/04/01.md

7.5 KiB

አሁን ሰንባላጥ

እዚህ ላይ ነህምያ አዲስ የታሪኩን አዲስ ክፍል መጀመሩን ለማመልት ሲል “አሁን” የሚለውን ቃል ይጠቀማል፡፡

ሰንባላጥ … ጦብያ

እነዚህ የወንድ ስሞች ናቸው፡፡ ይህ በነህምያ 2፡10 ላይ እንዴት እንደተተረጎሙ ይመልከቱ፡፡ (ስሞችን እንዴት መተርጎም ይቻላል የሚለውን ይመልከቱ)

በውስጡም እጅግ ነደደ፣ እጅግም ተበሳጨ

እዚህ ላይ “ነደደ” ተብሎ የተገለጸው አይሁዳውያን የፈረሰውን ቅጥር እያደሱ መሆኑን ሰንባላጥ መገንዘቡ ነው፡፡ ይህ ደግሞ የሰንባላጥ ንዴት እንደሚንድድ እሳት እንደሆነነ በጣም እንደተበሳጨ የሚያመለክት ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እጅግ በኃይል ተናደደ” ወይም “በጣም ተናደደ” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

በወንድሞቹ ፊት

“በዘመዶቹ ፊት” ወይም “በወገኖቹ ፊት”

እነዚህ ደካሞች መምድን ናቸው … ያድኑታልን … ይሰዋሉን … ስራውን በአንድ ቀን ይጨርሳሉን

ሰንባላጥ እነዚህን ጥያቄዎች የሚጠይቀው በአይሁዳውያን ላይ ለመሳለቅ ነው፡፡ እነዚህ በዓርፍተ ነገር መልክ ሊጻፉ ይችላሉ፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እነዚህ ደካማ አይሁዳውያን ምንም ነገር ሊያሳኩ አይችሉም፡፡ ከተማቸውን ከጥፋት አድነው ለራሳቸው ሊያደርጉ አይችሉም፡፡ መስዋዕት አያቀርቡም፡፡ (መልስ የማይሰጥባቸው ጥያቄዎች የሚለውን ይመልከቱ)

ደካማ አይሁዶች

“አቅመ ቢስ አይሁዶች”

በአንድ ቀን

በአንድ ቀን ስራው ሊያልቅ አይችልም ሲል አንድን ነገር ቶሎ ሰርቶ መጨረስ አለመቻልን ለማሳየት ነው፡፡” አማራጭ ትርጉም፡- “በቶሎ” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ድንጋዮቹ ከተቃጠሉ በኋላ ከፍርስራሽ ክምር መካከል ነፍስ ይዘሩባቸው ይሆን?

ሰንባላጥ ይህንንም ጥያቄ የሚጠይቀው በአይሁዳውያን ላይ ለመሳለቅ ነው፡፡ ይህ በዓርፍተ ነገር መልክ ሊጻፍ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ከተቃጠለው የፍርስራሽ ክምር መካከል ለድንጋዮቹ እንደገና ነፍስ ሊዘሩባቸው አይችሉም፡፡” (መልስ የማይሰጥባቸው ጥያቄዎች የሚለውን ይመልከቱ)

ድንጋዮቹ ከተቃጠሉ በኋላ ከፍርስራሽ ክምር መካከል ነፍስ ይዘሩባቸዋል

ይህ ሰዎቹ ከተማውን ነፍስ እንደዘሩበት ያህለ ደግመው ስለመስራታቸውና ስለመገንባታቸው ይናገራል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ከተቃጠሉትና ወደ ፍርስራሽነት ከተለወጡት የማይጠቅሙ ድንጋዮች ከተማይቱን ያድሳሉ ደግሞም ቅጥሩን እንደገና ይሰራሉ፡፡” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ከተቃጠሉ በኋላ የፍርስራሽ ክምር ከሆኑት

ይህ በገቢር/አድራጊ ቅርጽ መጻፍ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ሰዎች አቃጥለው የፍርስራሽ ክምር ካደረጉት ድንጋይ” (ገቢር/አድራጊ ወይም ተገብሮ/ተሳቢ የሚለውን ይመልከቱ)

በሚገነቡት ላይ ቀበሮ ቢወጣበት የድንጋይ ቅጥራቸውን ያፈርሰዋል

ሰንባላጥ የሚሰራው ቅጥር ደካማ እንደሆነ ለማሳየትና በእነርሱ ላይ ለመሳለቅ ቀበሮ ቢወጣበት እንደሚያፈርሰው ግነት በተሞላበት ንግግር ይናገራል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “የሚገነቡት ቅጥር በጣም ደካማ ከመሆኑ የተነሳ ትንሽ ቀበሮ እንኳን ቅጥሩ ላይ ቢወጣ የድንጋዩ ቅጥራቸው ይፈራርሳል፡፡” (ግነትና ጅምላ መግለጫየሚለውን ይመልከቱ)

አምላካችን ሆይ ስማ … ሰራተኞቹን አበሳጭተዋልና

እዚህ ላይ ነህምያ ወደ እግዚአብሔር ይጸልያል፡፡ ይህ በግልጽ ሊብራራና በትምህርተ ጥቅስ ሊጻፍ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ ከዚያም ጸለይሁ፣ “አምላካችን ስማ … ሰራተኞችን አስቆጥተዋቸዋልና፡፡ ስለዚህም …” (ግምታዊ እውቀትና ያለተገለጸ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

እኛ ተንቀናልና አምላካችን ስማ

እዚህ ላይ “እኛ” የሚለው ቃል የሚያመለክተው አይሁዳውያንን ነው፡፡ ይህ በዓረፍተ ነገር ቅርጽ መጻፍ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ጠላቶቻችን ንቀውናልና አምላካችን ስማ” (ገቢር/አድራጊ ወይም ተገብሮ/ተሳቢ የሚለውን ይመልከቱ)

ለብዝበዛ አሳልፈህ ስጣቸው

ይህ በገቢር/አድራጊ ቅርጽ መጻፍ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ጠላቶቻቸው እንዲበዘብዙአቸው አድርግ” (ገቢር/አድራጊ ወይም ተገብሮ/ተሳቢ የሚለውን ይመልከቱ)

ስድባቸውን በራሳቸው ላይ መልስባቸው

“ስድባቸውን” የሚለው ቃል የሚያመለክተው የሰንባላጥና የጦብያን ስድብ ነው፡፡ “በራሳቸው ላይ” የሚለው ሐረግ የሚያመለክተው ጠቅላላ ሕዝቡን ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ስድባቸው በራሳቸው ላይ ይሁንባቸው” ወይም “ስድባቸው በራሳቸው ላይ መሳለቂያ እንዲሆኑ ያድርጋው፡፡” (ተዛምዶአዊ የሚለውን ይመልከቱ)

አትክደን

ይህ በአካል ሊከደኑ እንደሚችሉ እቃዎች እንዲሁ የአንድ ሰው ኃጢአት እንደሚከደንና ይቅር እንደሚባል ያመለክታል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ይቅር አትበል” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

በደላቸውም በፊትህ አትደምሰስ

ይህ ሊሰረዝ እንደሚችል አንድ ጽሑፍ የአንድን ሰው ኃጢአት እንደሚወገድና እንደሚረሳ የሚያሳይ ው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “በደላቸውን አትርሳ”

የሚገነቡትን ሰዎች አበሳጭተዋልና

“ገንቢዎቹን አናድደዋቸዋል”

ቅጥሩንም ሰራን

“ቅጥሩን ደግመን ገነባን”

ቅጥሩም በሙሉ እስከ ቁመቱ አጋማሽ ድረስ ተጋጠመ

ይህ በገቢር/አድራጊ ቅርጽ ሊጻፍ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ቅጥሩን አንድ ላይ አጋጠምነው፤ ከጠቅላላ ቁመቱም ግማሹን ያህል ነበር” (ገቢር/አድራጊ ወይም ተገብሮ/ተሳቢ የሚለውን ይመልከቱ)

ግማሽ ቁመት የሚያክል

“እኩሌታ” ማለት ከሁለት ሁለት እኩያ መጠን ካላቸው ነገሮች አንዱ ማለት ነው፡፡ (ክፍልፋዮች የሚለውን ይመልከቱ)