am_tn/neh/03/28.md

2.1 KiB

ካህናት አደሱ … በቤታቸው አንጻር አደሱ … የምስራቁን በር .. አደሰ … ሌላውን ክፍል አደሱ … ትይዩውን አደሱ

እነዚህ ሐረጎች የሚያመለክቱት ስለ ቅጥሩ መታደስ ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ካህናት ቅጥሩን አደሱ … የቅጥሩን ክፍል አደሱ … የቅጥሩን የምስራቅ በር ክፍል አደሱ … የቅጥሩን ሌላ ክፍል አደሱ … የቅጥሩን ተቃራኒ ክፍል አደሱ” (አስጨምሬ የሚለውን ይመልከቱ)

ከፈረሱ በር በላይ

“በላይ” የሚለው ቃል እዚህ ጥቅም ላይ የዋለው የካህናቱ ቤት በከፍታ ከፈሱ በር በላይ ከፍ በሎ ይገኝ ሰለነበር ይመስላል፡፡

ከራሱ ቤት አንጻር

“ከራሱ ቤት ፊት ለፊት”

ከእነርሱ በኋላ … ከእርሱ በኋላ

“ከእነርሱ ቀጥሎ … ከእርሱ ቀጥሎ”

ሳዶቅ … ኢሜር … ሸማያ … ሴኬንያ … ሐናንያ … ሰሌምያ … ሐኖን … ሴሌፍ … ሜሱላም … በራክያ

እነዚህ የወንድ ስሞች ናቸው፡፡ (ስሞችን እንዴት መተርጎም ይቻላል የሚለውን ይመልከቱ)

የምስራቁ በር ጠባቂ የሴኬንያ ልጅ ሸማያ

የምስራቁ በር ጠባቂ የነበረው ሸማያ ነው፣ ሴኬንያ አልነበረም፡፡

የምስራቁ በር ጠባቂ

“የምስራቁን በር ይጠብቅ የነበረው ሰው” ወይም “የምስራቁን በር ይከፍትና ይዘጋ የነበረው ሰው”

ስድስተኛው ወንድ ልጅ

“ስድስተኛ የወንድ ልጅ” ወይም “በቁጥር ስድስተኛ የነበረው ወንድ ልጅ” (ደረጃ የሚያሳይ ቁጥር የሚለውን ይመልከቱ)

በጓዳው አንጻር

“አርሱ ይኖርበት ከነበረበት ክፍሎች ፊት ለፊት፡፡” “እርሱ” የሚለው ቃል የሚያመለክተው ሜሱላምን ነው፡፡