am_tn/neh/03/13.md

2.5 KiB

ሐኖን

ይህ የወንድ ስም ነው፡፡ (ስሞችን እንዴት መተርጎም ይቻላል የሚለውን ይመልከቱ)

የዛኖዋ ነዋሪዎች

“ከዛኖዋ የመጡ ሰዎች”

ዛኖዋ

ይህ የቦታ ስም ነው፡፡ (ስሞችን እንዴት መተርጎም ይቻላል የሚለውን ይመልከቱ)

የሸለቆ በር

“የሸለቆ በር” ወይም “ወደ ሸለቆ የሚወስደው በር፡፡” ይህን እንደ ማብራሪያ ሳይሆን እንደ ስም ለመተርጎም ይሞከር፡፡

በሮችዋን አስገቡ

“በሮችዋን አስገቡ” ወይም “በሮችን በቦታቸው አደረጉ”

መቀርቀሪያዎቹና መወርወሪያዎቹ

“ቁልፎቹንና መቀርቀሪያዎቹን፡፡” እነዚህ በሮቹ በአስተግንብኝ ሁኔታ ተዘግተው እንዲቆዩ ያደርጉ ነበር፡፡

እስከ ቆሻሻ መጣያ በሩ ድረስ አንድ ሺህ ክንድ የሚሆን ቅጥር አደሱ

ከሸለቆ በር እስከ ቆሻሻ መጣያ በር መካከል ያለውን የቅጥር ክፍል አደሱት፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ከሸለቆ በር እስከ ቆሻሻ መጣያ በር አንድ ሺህ ክንድ ርዝመት ያለው የቅጥር ክፍል አደሱ” (ግምታዊ እውቀትና ያለተገለጸ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

አንድ ሺህ ክንድ ርዝመት ያለው አደሱ

የኢየሩሳሌምን ቅጥር እያደሱ እንደነበር ግልጽ ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “አንድ ሺህ ክንድ ርዝመት ያለው የቅጥር ክፍል አደሱ” ወይም “ከሸለቆ በር ባሻገር ሌላ አንድ ሺህ ክንድ የቅጥሩን ክፍል አደሱ” (ግምታዊ እውቀትና ያለተገለጸ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

አንድ ሺህ ክንድ

“አንድ ሺህ ክንድ፡፡” ይህ በዘመናዊ የርዝመት መለኪያ ሊጻፍ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “460 ሜትር” (መጽሐፍ ቅዱሳዊ ርቀት እና ቁጥሮች የሚለውን ይመልከቱ)

ቆሻሻ መጣያ በር

ቆሻሻ ከከተማይቱ ይወገድ የነበረው በዚህ በር በኩል እንደነበር መገመት ይቻላል፡፡ ይህንን መግለጫ እንደ እንደ ማብራርያ ከመተርጎም ይልቅ እንደ ስም ለመተርጎም ይሞከር፡፡