am_tn/neh/02/19.md

1.5 KiB

ሰንባላጥ … ጦብያ

እነዚህ የወንድ ስሞች ናቸው፡፡ እነዚህን በነህምያ 2፡9-10 ላይ እንዴት እንደተተረጎሙ ይመልከቱ፡፡ (ስሞችን እንዴት መተርጎም ይቻላል የሚለውን ይመልከቱ)

ጌሳም

ይህ የወንድ ስም ነው፡፡ (ስሞችን እንዴት መተርጎም ይቻላል የሚለውን ይመልከቱ)

ምን እያደረጋችሁ ነው? ንጉሱ ላይ እያመጻችሁ ነውን?

እነዚህ መልስ የማይሰጥባቸው ጥያቄዎች ጥቅም ላይ የዋት ነህምያ ላይ ለመሳለቅ ነው፡፡ ይህ በዓርፍተ ነገር ቅርጽ ሊጻፉ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “የሞኝነት ስራ እየሰራችሁ ነው! በንጉሱ ላይ ልታምጹ አይገባም! (መልስ የማይሰጥባቸው ጥያቄዎች የሚለውን ይመልከቱ)

ንጉሱ

ይህ የሚያመለክተው የፋርስ ንጉስ አርጤክስስን ነው፡፡

ተነስተን እንሰራለን

ይህ ፈሊጥ ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም “እንደገና መገንባት እንጀምራለን” (ፈሊጥ የሚለውን ይመልከቱ)

እናንተ ግን በኢየሩሳሌም ድርሻ፣ መብትና የኛ የምትሉት የታሪክ መታሰቢያም የላችሁም

“እናንተ ግን በኢየሩሳሌም ምንም ድርሻ፣ ሕጋዊ መብት ወይም ሃይማኖታዊ ባለቤትነት የላችሁም“