am_tn/neh/02/17.md

1.6 KiB

ችግሩን ታያላችሁ

እዚህ ላይ “ታያላችሁ” የሚለው ቃል ብዙ ቁጥር ሲሆን ጥቅም ላይ የዋለው በነህምያ 2፡16 ላይ የተገለጹትን ሰዎች በሙሉ ለማመልከት ነው፡፡ (የሁለተኛ መደብ ቅርጾች የሚለውን ይመልከቱ)

በሮችዋ በእሳት ተቃጥለዋል

ይህ በገቢር/አድራጊ ቅርጽ ሊጻፍ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ጠላቶቻችን በሮችዋን በእሳት እንዴት እንዳቃጠሉት” (ገቢር/አድራጊ ወይም ተገብሮ/ተሳቢ የሚለውን ይመልከቱ)

ከእንግዲህ ወዲያ መሳለቂያ እንዳንሆን

“ከእንግዲህ ወዲያ እንዳናፍር”

የአምላኬ መልካሚቱ እጅ በእኔ ላይ ነበረች

የእግዚአብሔር “መልካሚቱ እጅ” የሚያመለክተው የእግዚአብሔርን “ሞገስ” ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “የእግዚአብሔር ሞገስ በእኔ ላይ ነበር” (ምትክ ስም የሚለውን ይመልከቱ)

እንነሳና እንስራ

ይህ ፈሊጥ ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “መገንባት እንጀምር” (ፈሊጥ የሚለውን ይመልከቱ)

ስለዚህ ለመልካም ስራ እጃቸውን አጠነከሩ

“እጃቸውን አጠነከሩ” የሚለው ሐረግ አንድን ስራ ለመስራት ተዘጋጁ ማለት ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ይህን መልካም ስራ ለመስራት ተዘጋጁ” (ፈሊጥ የሚለውን ይመልከቱ)