am_tn/neh/02/13.md

1.1 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡-

በዚህ ጉብኝቱ ጥቂት ሰዎች ከነህምያ ጋር አብረው ነበሩ፣ ነገር ግን ነህምያ የሚናገረው በአንደኛ መደብ ነው ምክንያቱም ቀዳሚው ሰው እርሱ ሰለነበር ነው፡፡ (አንደኛ፣ ሁለተኛና ሶስተኛ መደብ የሚለውን ይመልከቱ)

በምሽትም በሸለቆ በር ወጣሁ

“ሲመሽ፣ በሸለቆ በር በኩል ወጣሁ”

ቀበሮ

የበረሃ ውሻ

ቆሻሻ መጣያ በር

ይህ በር ቆሻሻ ከከተማው የሚወገድበት እንደነበር ይገመታል

ፈርሰው ክፍት የነበሩትን፣ የእንጨት በሮቹ ደግሞ በእሳት ተቃጥለው ነበር

ይህ በገቢር/አድራጊ ቅርጽ ሊጻፍ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “የእስራኤል ጠላቶች ሰብረው የከፈቱትን፣ ጠላቶቻቸው በእሳት አቃጥለው ያፈረሷቸውን የእንጨት በሮች፡፡ (ገቢር/አድራጊ ወይም ተገብሮ/ተሳቢ የሚለውን ይመልከቱ)