am_tn/neh/02/07.md

1013 B

ደብዳቤ ይሰጠኝ

ይህ በገቢር/አድራጊ ቅርጽ ሊጻፍ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ደብዳቤ ስጠኝ” (ገቢር/አድራጊ ወይም ተገብሮ/ተሳቢ የሚለውን ይመልከቱ)

ከወንዙ ማዶ ያለው ግዛት

ይህ ከኤፍራጥስ ወንዝ በስተ ምዕራብ በኩል የነበረው ግዛት ስም ነው፡፡ በሱሳ ከተማ ከነበረው ወንዝ ባሻገር ያለ ቦታ ነበር፡፡

አሳፍ

ይህ የአንድ ወንድ ስም ነው፡፡ (ስሞችን እንዴት መተርጎም ይቻላል የሚለውን ይመልከቱ)

የእግዚአብሔር መልካሚቱ እጅ በእኔ ላይ ነበረች

የእግዚአብሔር “መልካሚቱ እጅ” የሚያሳየው የእግዚአብሔርን “ሞገስ” ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “የእግዚአብሔር ሞገስ በእኔ ላይ ነበር” (ምትክ ስም የሚለውን ይመልከቱ)