am_tn/neh/02/01.md

1.7 KiB

በኒሳን ወር

“ኒሳን” በዕብራይስጥ የቀን መቁጠርያ የመጀመርያው ወር ስም ነው፡፡ (የዕብራይስጥ ወራቶች የሚለውን ይመልከቱ)

በንጉስ አርጤክስስ በሃያኛው አመት

“አርጤክስስ ንጉስ በሆነበት በ20ኛው አመት (ደረጃ የሚያሳይ ቁጥር የሚለውን ይመልከቱ)

አሁን

ይህ ቃል ጥቅም ላይ የዋለው ከዋናው የታሪክ ፍሰት ወጣ ብሎ ሌላ ነገር መጀመሩን ለማሳየት ነው፡፡ እዚህ ላይ ነህምያ በንጉሱ ፊት ስለነበረው መልክ የዳራ መረጃ ይሰጣል፡፡ (የዳራ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

ንጉሱ ግን

“ስለዚህም ንጉሱ”

ፊትህ ለምን አዘነ

እዚህ ላይ ነህምያ የተገለጸው በፊቱ ነው ምክንያቱም ፊት የሰውን ስሜት ሰለሚያሳይ ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ለምን አዘንህ” (ተዛምዶአዊ የሚለውን ተመልከት) (ወካይ ዘይቤ ይመልከቱ)

ይህ የልብ ሐዘን መሆን አለበት

ይህ ነህምያ ልቡ እንዳዘነ እርሱም እንደዛው እንዳዘነ ያሳያል፣ ምክንያቱም ልብ የስሜቶች ሁሉ ማዕከል እንደሆነ ተደርጎ ስለሚታሰብ ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “በጣም አዝነሃል” (ወካይ ዘይቤ ይመልከቱ)

ከዚያም እጅግ በጣም ፈራሁ

ነህምያ ንጉሱ ለጠየቀው ነገር መልስ ለመስጠት ሲዘጋጅ በጣም ፈራ ምክንያቱም ንጉሱ እንዴት እንደሚመልስለት አያውቅም ነበር፡፡