am_tn/neh/01/10.md

3.2 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡-

ነህምያ ጸሎቱን ቀጠለ፡፡

አሁን

ይህ ቃል ጥቅም ላይ የዋለው ነህምያ ወደ ሌላ የጸሎት ሃሳብ መሸጋገሩን ለማሳየት ነው፡፡ እዚህ ላይ ነህምያ በያሕዌ ተስፋ ቃል ላይ ተመስርቶ ጥያቄውን ያቀርባል፡፡

እነርሱ ባርያዎችህ ናቸው

“እነርሱ” የሚለው ቃል የሚያመለክተው እስራኤላውያንን ነው፡፡

በታላቅ ሃይልህና በብርቱ እጅህ

እዚህ ላይ “እጅህ” የሚለው ቃል ጥንካሬንና ሃይልን ያመለክታል፡፡ እነዚህ ሁለት ሐረጎች አንድ ላይ በመሆን የያሕዌን ሃይል ታላቅነት ለማጉላት ጥንድ ሃሳቦችን መስርተዋል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “በታላቅ ኃይልህ እና ከፍ ባለው ብርታትህ” ወይም “በጣም ኃያል በሆነው ብርታትህ” (ምትክ ስም እና ተመሳሳይ ጥንድ ሃሳብ የሚለውን ይመልከቱ)

የባርያህ ጸሎት

እዚህ ላይ “ባርያህ” የሚለው የሚያመለክተው ነህምያን ነው፡፡ አንድ ሰው ትህትና እና አክብሮት ለማሳየት ሲል ከአለቃው ጋር የሚነጋገረው እንዲህ ነበር፡፡ ነህምያ 1፡6ን እንዴት እንደተተረጎመ ይመልከቱ፡፡

የባርያዎችህ ጸሎት

እዚህ ላይ “ባርያዎችህ” የሚለው የሚያመለክተው ያህዌ ስለ ሕዝቡ እና ስለ ኢየሩሳሌም እንዲነሳ ይጸልዩ የነበሩትን የቀሩትን የእስራኤል ሕዝቦች በሙሉ ነው፡፡

ስምህን በማክበር ደስ የሚሰኙትን

እዚህ ላይ “ስም” የሚለው የሚያሳየው ያሕዌን ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “አንተን ለማክበር ደስ የሚሰኙትን” (ምትክ ስም የሚለውን ይመልከቱ)

በዚህ ሰው ፊት ምህረትን ስጠው

“ስጠው” የሚለው ቃል የሚያመለክተው ነህምያን ሲሆን በእግዚአብሔር ፊት ያለውን ትህትና ለመግለጽ ራሱን በሶስተኛ መደብ ያመለከተበት ነው፤ “በዚህ ሰው” የሚለው የሚያመለክተው የፋርስን ንጉስ አርጤክስስን ነው፡፡

በዚህ ሰው ፊት

ነህምያ የሚናገረው ንጉሱ በሚያይበት እይታ ላይ ተመስርቶ ስለ ንጉሱ ዝንባሌ ወይም አመለካከት ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ንጉሱ በእኔ ላይ ምህረቱን ያሳይ ዘንድ አድርግ” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

የንጉሱ ጠጅ አሳላፊ ሆኜ አገለግለው ነበር

ይህ ነህምያ በንጉሱ ቤተ መንግስት ምን ይሰራ እንደነበር የሚያሳይ የዳራ መረጃ ነው፡፡ የአንተ ቋንቋ የዳራ መረጃ የሚያሳዩበት የራሳቸው የተለየ መንገድ ሊኖረው ይችላል፡፡ (የዳራ መረጃ የሚለውን ተመልከት)