am_tn/neh/01/08.md

2.6 KiB

አገናኝ አርፍተ ነገር

ነህምያ ወደ እግዚአብሔር መጸለዩን ቀጠለ፡፡

እባክህ አስብ

“ማሰብ” የሚለው ፈሊጥ ማስታወስ የሚለውን ያመለክታል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እባክህ አስታውስ” (ፈሊጥ የሚለውን ይመልከቱ)

ለባርያህ ሙሴ ያዘዝከውን ቃልህን

“ያዘዝከውን” እና “ቃልህን” በሚሉት ቃላት ውስጥ ያሉት ተውላጠ ስሞች እግዚአብሔርን ያመለክታሉ፡፡

ታማኝ ባትሆኑ … እበትናችኋለሁ … ብትመለሱ … የእናንተን ሕዝብ

“እበትናችኋለሁ” እና “የእናንተ” የሚሉት ቃላት ተውላጠ ስሞች የብዙ ቁጥር መግለጫ ሲሆኑ የሚያመለክቱት ደግሞ እስራኤላውያንን ነው፡፡

በአሕዛብ መካከል እበትናችኋለሁ

ያሕዌ ሰው ዘርን ሲዘራ እንደሚበትን እንዲሁ እስራኤላውያንን በአሕዛብ መካከል እንዲኖሩ እንደሚበትናቸው ይናገራል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “በአሕዛብ መካከል እንድትኖሩ አደርጋችኋለሁ” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

የእናንተ ሕዝብ ተበትነው ቢሆኑም እንኳ

ይህ ዓርፍተ ነገር በገቢር ቅርጽ ሊገለጽ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ምንም እንኳ የእናንተ ሕዝብ ብበትናቸውም” (ገቢር/አድራጊ ወይም ተገብሮ/ተሳቢ የሚለውን ይመልከቱ)

እስከ ሰማይ ዳርቻ ደረስ

ያሕዌ በምድር ላይ በጣም ሩቅ ያሉትን ቦታዎች “እስከ ሰማይ ዳርቻ” ብሎ ይጠራቸዋል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “በጣም ሩቅ ወደሆኑ ቦታዎች” (ፈሊጥ የሚለውን ይመልከቱ)

ይኖርበት ዘንድ ወደ መረጥኩት ቦታ

ይህ ሐረግ የሚያመለክተው ቤተ መቅደሱ የሚገኝበትን ኢየሩሳሌምን ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “… ይኖርበት ዘንድ ወደ መረጥኩት ወደ ኢየሩሳሌም” (ግምታዊ እውቀት እና ያልተገለጸ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

ስሜ ይኖርበት ዘንድ ወደ መረጥኩት ቦታ

በዚህ ክፍል “ስሜ” የሚለው ቃል የሚያሳየው ራሱን ያሕዌን ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እኖርበት ዘንድ የመረጥኩት ቦታ” (ምትክ ስም የሚለውን ይመልከቱ)