am_tn/neh/01/06.md

1.3 KiB

ዓይኖችህ ይከፈቱ

“ተመልከተኝ፡፡” በዚህ ክፍል “ዓይኖችህ ይከፈቱ” የሚለው ሀሳብ በዘይቤአዊ መንገድ የተገለጸ ሲሆን ለአንድ ሰው ትኩረት መስጠትን የሚወክል ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ትኩረትህን በኔ ላይ አድርግ” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

የባርያህን ጸሎት ትሰማ ዘንድ

“እኔ ባርያህ፣ የምጸልየውን ጸሎት ትሰማ ዘንድ፡፡” “ባርያ” የሚለው ቃል የሚያመለክተው ነህምያን ነው፡፡ አንድ ሰው ትህትና እና አክብሮት ለማሳየት ሲል ከአለቃው ጋር የሚነጋገረው እንዲህ ነበር፡፡

ቀንና ለሊት

ይህን በማለቱ ቀንም ሌሊትም ይጸልያል፤ ነህምያ የጸሎቱን ድግግሞሽ አጉልቶ ያሳያል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ሁልጊዜ” (ወካይ ዘይቤ ይመልከቱ)

እኔና የአባቴ ቤት

በዚህ ክፍል “ቤት” የሚለው ቃል የሚያመለክተው ቤተሰብን ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እኔና ቤተሰቤ” (ምትክ ስም የሚለውን ይመልከቱ)