am_tn/neh/01/04.md

1.1 KiB

ከዚያም እንዲህ አልሁ

ነህምያ የተናገረው የጸለየውን ነገር ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ከዚያም ለያህዌ እንዲሀ አልሁ” (ግምታዊ እውቀት እና ያልተገለጸ መረጃ የሚለውን ተመልከት)

ያህዌ

ይህ እግዚአብሔር በብሉይ ኪዳን ራሱን ለሕዝቡ የገለጠበት የእግዚአብሔር ስም ነው፡፡ ስለ ያህዌ እና ይህን ቃል እንዴት መተርጎም እንደሚገባ ትራንስሌሽን ወርድ የሚለውን ድህረ ገጽ ተመልከት፡፡

እርሱን ለሚወድዱትና የእርሱን ትእዛዝ ለሚጠብቁ

ነህምያ የሚናገረው ለያህዌ ስለሆነ “እርሱ” እና “የእርሱ” የሚሉት ተውላጠ ስሞች “አንተ” እና “የአንተ” ተብለው ሊተረጎሙ ይችላሉ፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “አንተን ለሚወዱና የአንተን ትእዛዝ ለሚጠብቁ” (አንደኛ መደብ፣ ሁለተኛ መደብ እና ሦስተኛ መደብ የሚለውን ተመልከት)