am_tn/neh/01/03.md

1.0 KiB

እነርሱም እንዲህ አሉኝ

በዚህ “እነርሱም” የሚለው ቃል የሚያመለክተው አናኒ እና ከይሁዳ የመጡትን ሌሎች ጥቂት ሰዎችን ነው፡፡

ክፍለ ሀገር

በዚህ “ክፍለ ሀገር” የሚለው ቃል ይሁዳ በፋርስ ግዛት ስር የምትገኝ አንዲት የአውራጃ አስተዳደራዊ መዋቅር እነደሆነች ለማሳየት ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “የይሁዳ ክፍለ ሀገር” ወይም “ይሁዳ” (ግምታዊ እውቀት እና ያልተገለጸ መረጃ የሚለውን ተመልከት)

የኢየሩሳሌምም ቅጥር ፈርሶአል፥ በሮችዋም በእሳት ተቃጥለዋል

ይህ በገቢር ቅርጽ ሊገለጽ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ሰራዊቱ የኢየሩሳሌምን ቅጥር አፈራርሰውታል፣ በሮቿን ደግሞ አቃጥለውታል” (ገቢር/አድራጊ ወይም ተገብሮ/ተሳቢ የሚለውን ተመልከት)