am_tn/nam/03/18.md

2.0 KiB

እረኞችሽ አንቀላፍተዋል፤ ገዢዎችሽ አርፈው ተኝተዋል

እነዚህ ሁለት ሐረጎች ተመሳሳይ ትርጉም ይጋራሉ። ናሆም በጎቻቸውን እንደሚንከባከቡ እረኞች በመቁጠር ለአሦር መሪዎች ይናገራል። እርሱ ያንቀላፉ ይመስል ስለ እረኞቹና ስለ ገዢዎቹ ይናገራል። አ.ት፡ “እረኞች የሚመስሉ መሪዎቻችሁ ሞተዋል፤ ገዢዎቻችሁ በሙሉ ሞተዋል” (ተመሳሳይነት እና ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

ሕዝብሽ በተራሮች ላይ ተበትኗል

ናሆም እረኞቻቸው ከሞቱ በኋላ እንደተበተኑ በጎች ስለ ነነዌ ሕዝብ ይናገራል። አ.ት፡ “ሕዝብሽ እንደ በጎች በተራሮች ላይ ተበትነዋል”። (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

ቁስልሽ ሊፈወስ የማይችል ነው። ቁስልሽ የከፋ ነው

ንጉሡ በማይድን ቁስል የተሰቃየ ይመስል ናሆም የነነዌ መጥፋትና የንጉሥዋ ድል መደረግ የማይቀር መሆኑን ይናገራል። (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

ቁስልሽ ሊፈወስ የማይችል ነው

“ፈውስ” የሚለው ቃል በግሳዊ ሐረግ ሊተረጎም ይችላል። አ.ት፡ “ቁስልሽን ማንም ሊፈውስ አይችልም”። (የነገር ስም የሚለውን ተመልከት)

ከጽኑው ክፋትህ ያመለጠ ማነው?

ይህ የማሳመኛ ጥያቄ አጽንዖት የሚሰጠው አስቀድሞ በሚገምተው አሉታዊ ምላሽ ላይ ነው። በአሦር አቅራቢያ ይኖሩ የነበሩ ሕዝቦች ሁሉ ጽኑ በሆነው በአሦር ክፋት ምክንያት ተሰቃይተው ነበር። አ.ት፡ “ከጽኑው ክፋትህ ማንም ያመለጠ የለም”። (የማሳመኛ ጥያቄ የሚለውን ተመልከት)