am_tn/nam/03/14.md

2.7 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡

ናሆም ስለ ነነዌ ሕዝብ እነርሱ ከተማይቱን ራሷን እንደሆኑ አድርጎ መናገሩን ይቀጥላል። (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

ለከበባው ውሃ ለመቅዳት ሂጂ. . . ለጡቦቹ ጭቃ ርገጪ

ናሆም የሚናገረው ለነነዌ ሕዝብ ነው። ጠላት ከተማይቱን እንደሚያጠፋት ቢያውቅም ለጦርነት እንዲዘጋጁና ቅጥሮቹን እንዲጠግኑ ይነግራቸዋል። (ውስጠ ወይራ የሚለውን ተመልከት)

ታላላቅ ምሽጎቻችሁን አጠናክሩ

“ምሽጎቻችሁን ጠግኑ”

የሸክላ ዐፈር ፈልጊና ጭቃውን አቡኪ፤ ለጡቦቹ የሚሆን ቅርፅ አውጪ

እነዚህ ሐረጎች የከተማይቱን ቅጥር ለመጠገን የሚጠቀሙባቸውን የጭቃ ጡብ ስለመሥራታቸው ያመለክታል።

በዚያ እሳት ይበላሻል

እሳት ይባላ ይመስል ናሆም ስለሚያቃጥልና ስለሚያጠፋ እሳት ይናገራል። አ.ት፡ “በዚያ እሳት ያጠፋችኋል” ወይም “በዚያ ጠላቶቻችሁ በእሳት ያነዷችኋል”። (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

ሰይፍ ያጠፋሻል

ይህ “ሰይፍ” የሚለው ቃል ጠላቶቻቸው የሚያጠቁባቸውን ሰይፎች የሚያመለክት ፈሊጣዊ አነጋገር ነው። አ.ት፡ “ጠላቶቻችሁ በሰይፎቻቸው ይገድሏችኋል”። (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

የአንበጣ ኩብኩባ ሁሉን እንደሚበላ ይበላሻል

“እርሱ” የሚለው ቃል የሚገድላቸውን እንደሚበላ በሰውኛ የተነገረለትን “ሰይፍ” ያመለክታል። ወታደሮች ሰይፎቻቸውን በመጠቀም በነነዌ ያሉትን ሁሉ የሚገድሉበት ሁኔታ በመንገዱ ያገኘውን ሰብል ሁሉ ከሚበላው የአንበጣ መንጋ ጋር ተነጻጽሯል። አ.ት፡ “የአንበጣ መንጋ በመንገዱ ያገኘውን ሁሉ በቀላሉ እንደሚበላ የጠላቶቻችሁ ሰይፍ ሁላችሁንም ይገድላችኋል”። (ሰውኛ እና ተነጻጻሪ የሚለውን ተመልከት))

ራስሽን እንደ ኩብኩባ አርቢ፣ እንደ አንበጣም አብዢ

እነዚህ ቃላት ናሆም በነነዌ የሚኖረውን ሕዝብ ቁጥር በመንጋ ውስጥ ካሉት እጅግ ብዙ ቁጥር ካላቸው አንበጣዎች ጋር የሚያነጻጽርበትን አዲስ አንቀጽ ይጀምራሉ።