am_tn/nam/03/08.md

2.3 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡

ናሆም ከተማው ራሱ እነርሱን እንደሆነ አድርጎ ለነነዌ ሕዝብ ይናገራል። (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

አንቺ ከራሷ ከቲቤስ ትሻያለሽ?

ናሆም አስቀድሞ ለተገመተው አሉታዊ ምላሽ አጽንዖት ለመስጠት ይህንን የማሳመኛ ጥያቄ ይጠይቃል። አ.ት፡ “አንቺ ከቲቤስ ከራስዋ አትሻይም”። (የማሳመኛ ጥያቄ የሚለውን ተመልከት)

ቲቤስ

ይህ አሦራውያን ድል አድርገዋት የነበረችው የግብፅ የቀድሞዋ ዋና ከተማ ነበረች። (‘ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ’ የሚለውን ተመልከት)

በዐባይ ወንዝ ዳር የተሠራች ነበረች

“በዐባይ ወንዝ ዳር የተቋቋመች ነበረች”

ውቅያኖሱ መከላከያዋ የነበረ፣ ባህሩ ራሱም ግድግዳዋ የነበረ

እነዚህ ሁለት ሐረጎች ተመሳሳይ ትርጉም ይጋራሉ። “ውቅያኖስ” እና “ባህር” የሚሉት ቃላት ሁለቱም በከተማይቱ አጠገብ የሚፈሰውን የዐባይን ወንዝ ያመለክታሉ። አ.ት፡ “አንዳንድ ከተሞች ለራሳቸው ቅጥር እንዳላቸው ሁሉ የዐባይ ወንዝ መከላከያዋ ነበር”። (ዘይቤአዊ አነጋገር እና ተመሳሳይነት የሚለውን ተመልከት)

“ኩሽና ግብፅ ጉልበቶቿ ነበሩ

“ኢትዮጵያና ግብፅ አበረቷት” ወይም “ኩሽና ግብፅ ተባባሪዎቿ ነበሩ”

ለእርሱ ፍጻሜ አልነበረውም

“እርሱ” የሚለው ቃል ኩሽና ግብፅ ለቲቤስ የሰጧትን “ጉልበት” ያመለክታል። ለእርሱ ፍጻሜ አልነበረውም ሲል እጅግ ታላቅ የሆነውን ጉልበት የሚገልጽ ግነት ነው። አ.ት፡ “ኃይላቸው እጅግ ታላቅ ነበር”። (ግነት እና ማጠቃለያ የሚለውን ተመልከት)

ፉጥና ሊቢያ

እነዚህ ለቲቤስ ቅርብ የሆኑ በሰሜን አፍሪካ የሚገኙ የቦታ ስሞች ናቸው። (‘ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ’ የሚለውን ተመልከት)