am_tn/nam/03/01.md

1.3 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡

ናሆም አብዛኛውን ጊዜ ትንቢቱን የጻፈው በግጥም መልክ ነው። የዕብራይስጥ ግጥም የተለያዩ ተመሳሳይነትን ይጠቀማል። እዚህ ጋ የነነዌን ጥፋት መግለጹን ይቀጥላል። (ግጥም እና ተመሳሳይነት የሚለውን ተመልከት))

በደም የተሞላች ከተማ

እዚህ ጋ “ደም” የሚለው ቃል የሚወክለው ደም ማፍሰስን ሲሆን ነፍስ ያጠፉትን ሰዎች ያመለክታል። አ.ት፡ “በነፍሰ ገዳዮች የተሞላች ከተማ”። (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

ሐሰትን ሁሉ የተሞላ ነው

እዚህ ጋ “ሐሰት” የሚለው ቃል ውሸትን ለሚናገሩ ፈሊጣዊ አነጋገር ነው። አ.ት፡ “በውሸተኞች የተሞላ ነው”። (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

የጅራፍ ድምፅና የሚንገጫገጭ መንኩራኩር ጩኸት፣ የፈረሶችና የሰረገላዎች ዝላይ

እነዚህ ሐረጎች ፈረሶቹን በመግረፍ የሚነዷቸው ሰዎች በጎዳናዎቹ በሚገሰግሱበት ጊዜ የሰረገላዎቹን ድምፅ የሚገልጹ ናቸው።