am_tn/nam/02/13.md

2.5 KiB

እነሆ፣ እኔ በእናንተ ላይ ነኝ

እዚህ ጋ እግዚአብሔር መናገር ይጀምራል

እነሆ

“ተመልከቱ” ወይም “አድምጡ” ወይም “የምነግራችሁን ልብ በሉ”።

ደቦል አንበሶቻችሁን ሰይፍ ይበላቸዋል

እዚህ ጋ “ሰይፍ” የሚለው ቃል በሰይፍ የሚዋጉትን ወታደሮች የሚያመለክት ሲሆን ንጥቂያውን ሰው እንደሚበላው ዓይነት ተደርጎ ተነግሯል። ናሆም ደግሞ የነነዌን ሕዝብ እንደ አንበሶች በመቁጠር መናገሩን ቀጥሏል። አ.ት፡ “ተዋጊዎች ሰዎቻችሁን በሰይፍ ይገድላሉ” (ፈሊጣዊ አነጋገር፣ ሰውኛ እና ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

የምትገድሉትን እንስሳ ከምድራችሁ አጠፋለሁ

እግዚአብሔር ሕዝቦችን በሚያድኑ አንበሶች ስለተመሰሉት የነነዌ ሰዎች ይናገራል። አማራጭ የሚሆኑት ትርጉሞች፣ 1) “የሚገደል እንስሳ” የሚሉት ቃላት ካጠቋቸው ላይ የወሰዷቸውን ነገሮች የሚያመለክት ዘይቤአዊ አነጋገር ሲሆን የሚገድሉትን እንስሳ እንደሚያጠፋባቸው ሁሉ እግዚአብሔር እነዚያን ነገሮች ከእነርሱ እንደሚወስድባቸው ይናገራል ወይም 2) ታዳኞቻቸው የሆኑ ይመስል የነነዌ ሕዝብ ስለበዘበዟቸው ሕዝቦች እግዚአብሔር ይናገራል፣ እርሱ የሚገድሉትን እንስሳ በሚያጠፋባቸው መልኩ በተጨማሪ ሌሎች ሕዝቦችን እንዳይበዘብዙ ይከለክላቸዋል። አ.ት፡ “ሌላ የትኛውንም ሕዝብ እንዳትገድሉ እከለክላችኋለሁ”። (ዘይቤአዊ እና ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

ከእንግዲህ የመልዕክተኞቻችሁ ድምፅ አይሰማም

ይህ አሦራውያን በሌሎች ሕዝቦች እጅ እንዲሰጧቸው ወይም እንዲገብሩላቸው ለመጠየቅ የሚልኳቸውን መልዕክተኞች ሳያመለክት አይቀርም። ይህ በገቢራዊነት ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “ዳግመኛ የመልዕክተኞቻችሁን ድምፅ የሚሰማ አይኖርም”። (ገቢራዊ ወይም ተገብሮአዊ የሚለውን ተመልከት)