am_tn/nam/02/03.md

2.3 KiB

የኃያላኑ ጋሻ ቀይ ነው

አማራጭ ትርጉሞቹ 1) ጋሻዎቹ በብረት ገጽታቸው ላይ የፀሐይ ብርሃን በሚያንጸባርቅበት ጊዜ ቀልተው ይታያሉ ወይም 2) ጋሻዎቹ በቀይ ቀለም በተነከሩ ቆዳዎች የተሸፈኑ ናቸው።

ኃያላኑ

ነነዌን “የሚረጋግጡ” እና “ብትንትኗን የሚያወጡ” ወታደሮች ናቸው (ናሆም 2፡1)

ሰረገሎቹ በብረቶቻቸው ያብረቀርቃሉ

ይህ የሚያመለክተው ከብረት በተሠሩት ሰረገላዎች ላይ የፀሐይ ብርሃን ማንጸባረቁን ሳይሆን አይቀርም።

እንዲዘጋጁ በተደረጉበት በዚያን ቀን

ይህ በገቢራዊነት ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “ወታደሮቹ ባዘጋጇቸው ጊዜ” ወይም “ወታደሮቹ እንዲዋጉ ባዘጋጇቸው ጊዜ”። (ገቢራዊ ወይም ተገብሮአዊ የሚለውን ተመልከት)

እጀታቸው ከጥድ መሳይ ዛፍ የተሠሩ ጦሮች በአየር ላይ ይወዛወዛሉ

ይህ በገቢራዊነት ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “ወታደሮቹ ጦራቸውን በአየር ላይ ያወዛውዛሉ” (ገቢራዊ ወይም ተገብሮአዊ የሚለውን ተመልከት)

ጥድ መሳይ ዛፍ

እንጨቱ ለጦር መሳሪያነት የሚመረጥ የዛፍ ዓይነት ነው። (ያልታወቁትን መተርጎም የሚለውን ተመልከት)

ሰረገሎቹ በየጎዳናው ይፈጥናሉ

“ወታደሮቹ ሰረገላዎቹን በጎዳናዎቹ ላይ በስድነት ይነዷቸዋል”

ፋና ይመስላሉ

ናሆም በሰረገላዎቹ ላይ የሚንጸባረቀውን የፀሐይ ብርሃን የእሳት ብርሃን ከሚሰጠው ፋና ጋር ያነጻጽረዋል። (ተነጻጻሪ የሚለውን ተመልከት)

እንደ መብረቅ ይሮጣሉ

ናሆም በሰረገላዎቹ ላይ የሚንጸባረቀውን የፀሐይ ብርሃንና ሰረገላዎቹ የሚያደርጉትን ፈጣን እንቅስቃሴ በሰማይ ላይ በፍጥነት ከሚንጸባረቀው መብረቅ ጋር ያነጻጽራል። (ተነጻጻሪ የሚለውን ተመልከት)