am_tn/nam/02/01.md

4.7 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡

ናሆም አብዛኛውን ጊዜ ትንቢቱን በግጥም መልክ ይጽፋቸው ነበር። የዕብራይስጡ ግጥም የተለያዩ ተመሳሳይነቶችን ይጠቀማል። እዚህ ጋ የነነዌን መጥፋት መተረክ ይጀምራል። (ግጥም እና ተመሳሳይነት የሚለውን ተመልከት)

አንቺን ረጋግጦ የሚያደቅሽ እርሱ

“አንቺ” የሚለው ቃል ነነዌን ያመለክታል። ናሆም የሸክላ ማሰሮን እንደሚሰባብር ነነዌን በመሰባበር ስለሚያጠፋ ሰራዊት ወይም ወታደራዊ መሪ ይናገራል። አ.ት፡ “አጥፊሽ” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

አንቺን የሚረጋግጥሽ እርሱ

“እርሱ” የተባለው ሰው ግልጽ አይደለም፣ ስለዚህ የወል ቃል በመጠቀም ተርጉም። አ.ት፡ “አንድ አንቺን የሚሰባብርሽ”

በአንቺ ላይ እየመጣ ነው

“በአንቺ ላይ ይመጣል” የሚለው አነጋገር ሊያጠቃሽ ማለት ነው። አ.ት፡ “ሊያጠቃሽ ተዘጋጅቷል” (አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

በከተማው ቅጥር ላይ ሰዎችን አቁሚ፣ መንገዶችሽን ጠብቂ፣ ራስሽን አበርቺ፣ ሰራዊትሽን ሰብስቢ

ናሆም ለነነዌ ሕዝብ ይናገራል። ጠላት ከተማይቱን እንደሚያጠፋት ቢያውቅም ለጦርነት እንዲዘጋጁ ይነግራቸዋል። (ምጸት የሚለውን ተመልከት)

በከተማው ቅጥር ላይ ሰዎችን አቁሚ

ነነዌ የሚከባት ሰፊና ጠንካራ ቅጥር ነበራት። ይህ አጥቂዎችን ለመዋጋት ወታደሮችን በግምቡ ጫፍ ላይ ማስፈር መቻላቸውን ያመለክታል። አስፈላጊ ከሆነ ይህንን ጠቅለል ባለ ሐረግ መተርጎም ይቻላል። አ.ት፡ “በምሽጎችሽ ላይ ሰው አኑሪ” ወይም “መከላከያሽን አዘጋጂ” (የተገመተ ዕውቀትና የተሰወረ መረጃ የሚለውን ተመልከት)

መንገዶችሽን ጠብቂ

ይህ ጠላት እንዳይቀርባቸው ለመከላከል ወደ ከተማይቱ የሚወስደውን መንገድ በወታደሮች ማስጠበቅን ያመለክታል።

ራስሽን አበርቺ

ይህ ፈሊጣዊ አነጋገር ሲሆን ትርጉሙም ራስን ለተግባር ማዘጋጀት ማለት ነው። እዚህ ጋ ቃሉ ለወታደራዊ ተግባር ጥቅም ላይ ውሏል። አ.ት፡ “ራስሽን ለጦርነት አዘጋጂ” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

እግዚአብሔር እንደ እስራኤል ግርማ ሁሉ የያዕቆብን ግርማ ያድሳል

“ያዕቆብ” እና “እስራኤል” የሚሉት ቃላት ከያዕቆብ ለተወለዱት ሕዝቦች ጥቅም ላይ የዋለ ፈሊጣዊ አነጋገር ነው። አማራጭ ሊሆኑ የሚችሉት ትርጉሞች፣ 1) “ያዕቆብ” የሚለው ቃል የደቡቡን መንግሥት እና “እስራኤል” የሚለው የሰሜኑን መንግሥት ያመለክታል። አ.ት፡ “የእስራኤልን ግርማ ለማደስ ቃል እንደገባ ሁሉ የይሁዳንም ግርማ ያድሳል” ወይም 2) “ያዕቆብ” እና “እስራኤል” ሁለቱም የሚያመለክቱት የሰሜኑና የደቡቡ መንግሥት ተደምረውና ሁለቱ የግጥም መስመሮች ተመሳሳይ ሆነው መላውን ሕዝብ ነው። (ፈሊጣዊ አነጋገር እና ተመሳሳይነት የሚለውን ተመልከት)

ዘራፊዎቹ

በተለይ በጦርነት ጊዜ አንዳንድ ነገሮችን በኃይል አስገድደው የሚሰርቁ ሰዎች

የወይን ቅርንጫፎቻቸውን አጥፍተዋል

አማራጭ የሚሆኑት ትርጉሞች 1) እስራኤል ቅርንጫፎቹን አሦራውያን ገነጣጥለው ባዶውን እንዳስቀሩት ወይን አሦራውያን ንብረታቸውን አስገድደው መውሰዳቸውን የሚያመለክት ዘይቤአዊ አነጋገር ነው። አ.ት፡ “ያለ ቅርንጫፍ እንደ ቀረ ወይን ንብረታቸውን ዘርፈዋቸዋል” ወይም 2) “የወይን ቅርንጫፎች” የሚሉት ቃላት በየአገራቱ ለእርሻ በሚውሉ መስኮች ላይ ናቸው። አ.ት፡ “የሰብል ማሳዎቻቸውን አጠፉ” (ዘይቤአዊ እና ምሳሌአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)