am_tn/mic/07/18.md

1.5 KiB

ርስታቸውን … የሚወስድ እንዳንተ ያለ አምላክ ማነው?

ሚክያስ እንደ እግዚአብሔር ያለ ሌላ አምላክ እንደሌለ አጽንዖት ይሰጣል። ይህ እንደ መግለጫ ሊተረጎም ይችላል። አ.ት፡ “ርስትን … የሚወስድ እንዳንተ ያለ አምላክ እንደሌለ አውቃለሁ”።

የርስቱን ትሩፋን

“እነዚያ ከቅጣቱ የተረፉ የእርሱ ምርጥ ሕዝቦች”

አንተ … የርስቱ ትሩፍ? እርሱ በቃል ኪዳን ታማኝነቱ ደስ ስለሚሰኝ ለዘላለም አይቆጣም

እዚህ ጋ “የእርሱ” እና “እርሱ” የሚሉት ቃላት በሁለተኛ መደብ ሊነገሩ ይችላሉ። አ.ት፡ “አንተ … የርስትህ ትሩፍ፣ ለዘላለም የማትቆጣው በቃል ኪዳን ታማኝነትህ ደስ ስለምትሰኝ ነው?” ወይም “አንተ … የርስትህ ትሩፍ ነህ? በቃል ኪዳን ታማኝነትህ ደስ ስለሚልህ ለዘላለም አትቆጣም”

በቃል ኪዳን ታማኝነቱ ደስ ይለዋል

“ታማኝነት” የሚለው የነገር ስም “ታማኝ” ተብሎ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “ለቃል ኪዳኑ ታማኝ በመሆን ደስ ይለዋል” ወይም “ለሕዝቡ ታማኝ በመሆኑ ደስ ይለዋል”

ያልፈዋል

ይተወዋል

ቁጣውን አይጠብቅም

“ተቆጥቶ አይቆይም”