am_tn/mic/07/14.md

1.4 KiB

ሕዝብህን በበትርህ ጠብቅ፣ የርስትህንም መንጋ

ሚክያስ ወገኖቹን የእስራኤልን ሕዝብ እንደገና እንዲጠብቃቸው በመጠየቅ ወደ እግዚአብሔር ይጸልያል። እረኛ በጎቹን ለመጠበቅና ለመምራት አርጩሜ እንደሚጠቀም ሁሉ እዚህ ጋ “በትር” የእግዚአብሔርን መሪነትና ምሪት ሰጪነት ያመለክታል። (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

በጥሻ ውስጥ ለብቻቸው ይኖራሉ፣ በለመለመው መስክ መካከል

ሚክያስ የሚመገቡት ብዙ ሣር ባለበት መስክ እንደሚግጡ ከብቶች ሳይሆን በጫካ ውስጥ እንደሚደበቁ የዱር እንስሳት መስሎ ሕዝቡን ይናገራል። (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

ጥሻ

አንስተኛ እንጨት ያላቸው ዕጽዋት የሚያድጉበት ስፍራ

ባሳንና ገለዓድ

እነዚህ አካባቢዎች የምግብ እህል ለማብቀል ለም መሬት በመሆናቸው ይታወቃሉ

እንደ ቀደመው ዘመን

ዳዊት ንጉሥ በነበረበት ጊዜ፣ ከብዙ ዓመታት በፊት ባሳንና ገለዓድ የእስራኤል ክፍል ነበሩ

እንደ ቀድሞው … ተአምራትን

እግዚአብሔር ለሕዝቡ ይናገራል።