am_tn/mic/07/11.md

1.5 KiB

ቅጥሮቻችሁን የምትሠሩበት ጊዜ ይመጣል

እዚህ ጋ “ቅጥሮች” የሚያመለክተው ከጠላቶቻቸው ጥበቃና ደህንነት ያገኙባቸውን በከተሞቻቸው ዙሪያ ያሉትን ቅጥሮች ነው።

ዳርቻዎችሽ እስከ ሩቅ ድረስ ይስፋፋል

ይህ በገቢራዊነት ሊተረጎም ይችላል። አ.ት፡ “እግዚአብሔር ምድርሽን እጅግ ያሰፋዋል” ወይም “እግዚአብሔር የመንግሥትሽን ስፋት እጅግ ያበዛዋል”

ወንዙ

የወንዙን ስም ግልጽ ማድረግ ይኖርብህ ይሆናል። አ.ት፡ “የኤፍራጥስ ወንዝ”

ከባህር እስከ ባህር

የባህሮቹን ስም ግልጽ ማድረግ ይኖርብህ ይሆናል. “በምዕራብ ካለው ከሜዴትራንያን ባህር በስተምስራቅ እስካለው ሙት ባህር ድረስ”

ከተራራ እስከ ተራራ

“ከአንዱ ተራራ እስከ ሌላኛው”። ሚክያስ ስለ አንድ ስለ ታወቀ ተራራ አይናገርም።

ምድሪቱ ባድማ ትሆናለች

“ምድሪቱ ባዶ ትሆናለች” ወይም “በምድሪቱ ላይ ማንም አይኖርም”

በሥራቸው ፍሬ ምክንያት

ፍሬ የቀደመውን ሥራ ውጤት የሚያመለክት ዘይቤአዊ አነጋገር ነው። አ.ት፡ “ሥራቸው ባስከተለው ውጤት ምክንያት” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)