am_tn/mic/07/10.md

1.8 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡

ሚክያስ አንዲት ሴት ጠላቷ ለሆነች ለሌላይቱ ሴት በምትናገርበት መልኩ መናገሩን የቀጠለበትንና በምዕራፍ 7፡8 የጀመረውን ግጥም ይጨርሳል። ይህቺ ምናልባት የእስራኤል ሕዝብ የምትወክለው፣ “ለወታደሮቹ ሴት ልጅ” የምትናገር (ሚክያስ 5፡1)፣ እስራኤልን ወግተው የነበሩትን አገሮች የምትወክል የጽዮን ሴት ልጅ ትሆን ይሆናል (ሚክያስ 1፡13)። (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

አምላክህ … ያለች ጠላቴ … ዓይኖቼ

“ጠላቴ”፣ “ያለች”፣ “ያንተ”፣ እና “የእኔ” የሚሉት ቃላት እዚህ ጋ የሚያመለክቱት በግጥሙ ውስጥ ያለችውን ሴት ሲሆን አነስታይ ነጠላ ቁጥር ነው።

አምላክህ እግዚአብሔር ወዴት ነው?

ጠላት በእስራኤል ሕዝብ ላይ ለመሳለቅ በጥያቄ ይጠቀማል። እንደ መግለጫ ሊተረጎም ይችላል። አ.ት፡ “አምላክህ እግዚአብሔር ሊረዳህ አይችልም”።

ዓይኖቼ

በዚህ ስፍራ ቃሉ የሚያመለክተው የሰውን ሁለንተና ነው። አ.ት፡ “እኔ” ወይም “እኛ”።

ትረገጣለች

ይህ በገቢራዊነት ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “ጠላቶቿ ይረግጧታል”

በመንገድ እንዳለ ጭቃ

አንዳች ክፉ እንደሚያደርጉ ሳያስቡ በጭቃ ላይ እንደሚሄዱ ሰዎች የእስራኤልን ጠላቶች አንዳች ክፉ እንደሚያደርጉ ሳያስቡ ከሚያጠፉ ጋር ተነጻጽረዋል።