am_tn/mic/07/09.md

1.2 KiB

ቁጣውን እታገሳለሁ

ቁጣ ሚክያስ በእግዚአብሔር ተገዶ እንደ ተሸከመው ጠጣር ነገር ተደርጎ ተነግሯል። አ.ት፡ “እርሱ ስለተቆጣኝ እሰቃያለሁ” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

ስለ ጉዳዬ እስኪሟገትልኝና እስኪፈርድልኝ ድረስ

የእስራኤልን ሕዝብ የጎዱትን ሌሎች ሕዝቦች እግዚአብሔር ይቀጣቸዋል።

ይሟገትልኛል

እግዚአብሔር በፍርድ ቤት ለሚክያስ እንደሚከላከልለት ሆኖ ተነግሮለታል። አ.ት፡ “ከሚጎዱኝ ያድነኛል” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

ይፈርድልኛል

“ፍትሕን ያመጣልኛል”

ወደ ብርሃን ያመጣኛል

ሚክያስን ከጨለማ (ሚክያስ 7፡8) ወደ ብርሃን ማምጣት በመከራው ምክንያት መሰቃየቱ ማብቃቱንና በሰላም ሊኖር መቻሉን የሚያመለክት ዘይቤአዊ አነጋገር ነው። (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

በፍትሑ ይታደገኛል

“ፍትሕን ያመጣልኛል፣ ይታደገኛልም”