am_tn/mic/07/07.md

1.7 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡

ሚክያስ በቁጥር 8 ላይ አንዲት ሴት ጠላቷ ለሆነች ለሌላይቱ ሴት በምትናገርበት መልኩ መናገር ይጀምራል። ይህቺ ምናልባት የእስራኤል ሕዝብ የምትወክለው፣ “ለወታደሮቹ ሴት ልጅ” የምትናገር (ሚክያስ 5፡1)፣ እስራኤልን ወግተው የነበሩትን አገሮች የምትወክል የጽዮን ሴት ልጅ ትሆን ይሆናል (ሚክያስ 1፡13)። በእንግሊዝኛው “ዩ” ያሉበት ትዕዛዛቱና ምሳሌዎቹ ሁሉ አነስታይ ጾታ ነጠላ ቁጥር ነው።

ለእኔ ግን

እዚህ ጋ “እኔ” የሚያመለክተው ሚክያስን ነው።

የድነቴን አምላክ እጠብቃለሁ

“ድነት” የሚለው የነገር ስም እንደ ግሥ ሊተረጎም ይችላል። አ.ት፡ “የሚያድነኝን እግዚአብሔርን እጠብቃለሁ” ወይም “አዳኙን እግዚአብሔርን እጠብቃለሁ”።

ይሰማኛል

“መስማት” የሚለው ቃል መስማትንና ማድረግን ይወክላል። አ.ት፡ “ሊረዳን ይነሣል”

መውደቅ …መነሣት

እነዚህ ቃላት በአደጋ ምክንያት መከራንና ከዚያ ማገገምን የሚያመለክቱ ዘይቤአዊ አነጋገሮች ናቸው። (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

በጨለማ መቀመጥ

እነዚህ ቃላት በአደጋ ምክንያት መከራ መሠቃየትን የሚያመለክቱ ዘይቤአዊ አነጋገሮች ናቸው። (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)