am_tn/mic/07/05.md

927 B

የትኛውንም ባልንጀራችሁን አትታመኑ … የገዛ ቤቱን ሰዎች

ሚክያስ ከእንግዲ በእግዚአብሔር ሕዝብ መካከል አንድም ደግ፣ ታማኝና ለእግዚአብሔር የሚገዛ እንደሌለ ማሳየቱን ቀጥሏል። እዚህ ጋ ጓደኞቻቸውን ወይም ቤተ ሰቦቻቸውን መታመን እንደማይችሉ አጽንዖት ይሰጣል።

ምራት በአማቷ ላይ

“ትነሣለች” የሚለው ቃል ቀደም ብሎ ካለው ሐረግ ምን ማለት እንደሆን መረዳት ይቻላል። እዚህም ሊደገሙ ይችላሉ። አ.ት፡ “ምራት በአማቷ ላይ ትነሣለች”።

የገዛ ቤቱ

“ቤት” የሚለው ቃል በቤቱ ውስጥ የሚኖሩ ቤተ ሰቦችን የሚያመለክት ፈሊጣዊ አነጋገር ነው። አ.ት፡ “የገዛ ቤተ ሰቡ”