am_tn/mic/07/03.md

1.4 KiB

እጆቻቸው በጣም ጥሩዎች ናቸው

እጅ የሰው ምሳሌ ነው። አ.ት፡ “ሕዝቡ በጣም ጥሩዎች ናቸው”።

ከእነርሱ እጅግ የተሻለው እንደ አሜከላ ነው፣ እጅግ ትክክለኛው ከእሾኽ ኩርንችት የከፋ ነው

አሜከላና እሾህ ለምንም የማይጠቅሙና የሚነካቸውን የሚጎዱ ናቸው። እስራኤላውያን ገዢዎች እና ፈራጆች አንዳች መልካም አላደረጉም፣ ሕዝቡንም ጎዱት።

እጅግ ትክክለኛው

“ከእነርሱ መልካም የሆነውን ለማድረግ የሚጥሩት”

በጠባቂዎቻችሁ አስቀድሞ የተነገራችሁ፣ የምትቀጡበት ቀን ይህ ነው

ሚክያስ ለእስራኤል ሕዝብ ይናገራል፣ ስለዚህ በሁለቱም ሁኔታ “የእናንተ” የሚለው ቃል ብዙ ቁጥር ነው። “ጠባቂ” የሚለው ቃል ነቢያትን የሚመለከት ዘይቤአዊ አነጋገር ነው። አ.ት፡ “ነቢያቶቻቸው እግዚአብሔር እንደሚቀጣቸው ነግረዋቸዋል”።

ግራ የሚጋቡበት ሰዓት አሁን ነው

የነገር ስም የሆነው “ግራ የሚጋቡበት” እንደ ግሥ ሊተረጎም ይችላል። አ.ት፡ “የሚሆነውን ነገር የማይረዱበት ጊዜ አሁን ነው”።