am_tn/mic/07/01.md

1.6 KiB

በበጋ የተሰበሰበውን ፍሬ፣ የተለቀመውንም ወይን መስያለሁ

ሚክያስ አጫጆች አጭደው ከጨረሱት በኋላ ምግብ የሚሆነውን እንደሚፈልግ ሰው ታማኝ ሰዎችን እንደፈለገ ነገር ግን አንድም ሰው እንዳጣ ይናገራል። ፍሬ ለመሰብሰብ የሚፈልገው ሰው አሳቡ በግልጽ መቀመጥ መቻል አለበት። አ.ት፡ “የበጋው ፍሬ ከተሰበሰበ በኋላ ፍሬ የሚፈልገውን፣ ወይኑ ከተለቀመም በኋላ ቃርሚያውን እንደሚለቅም ሰው መስያለሁ”።

የወይን ዘለላል የለም … የበሰለው የመጀመሪያ በለስ የለም

ሚክያስ ለመበላት ጥሩ እንደሆነ ፍሬ ታማኝና ትክክለኛ ስለሆኑ ሰዎች ይናገራል። (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

ታማኞች ሰዎች ከምድሪቱ ጠፍተዋል፤ አንድም ትክክለኛ የሆነ ሰው የለም … ሁሉም ደም ለማፍሰስ ያደባሉ፤ እያንዳንዱ ያጠምዳል

እነዚህ ግነቶች ናቸው። አ.ት፡ “ታማኞች ሰዎች ከምድሪቱ እንደ ጠፉ ይሰማኛል፣ ትክክለኛ ሰው የለም፣ ሁሉም ደም … የሚያደቡ ይመስለኛል፣ እያንዳንዱም ያጠምዳል።

ደም ለማፍሰስ

ደም የንጹሐንን ሞት የሚያመለክት ዘይቤአዊ አነጋገር ነው። አ.ት፡ “ንጹሐን ሰዎችን ለመግደል”