am_tn/mic/06/16.md

2.3 KiB

የዖምሪ ሥርዓትና የአክዓብ ቤት ሥራዎች ሁሉ ተጠብቀዋል

ይህ በገቢራዊነት ሊተረጎም ይችላል፣ አንተም ዋናውን ቃል የገደፉት በገደፉበት ቦታ ቃላቱን ማሟላት ይኖርብህ ይሆናል። አ.ት፡ “ዖምሪ ያዘዘውን ፈጽመሃል፣ የአክዓብ ቤት ያደረጋቸውን እነዚያኑ ነገሮች አድርገሃል”።

ዖምሪ … አክዓብ

ሁለቱም ሰዎች የሰሜናዊው የእስራኤል መንግሥት ነገሥታት ነበሩ። እግዚአብሔር ሁለቱም እጅግ ክፉዎች እንደነበሩ ተመልክቶአል።

የአክዓብ ቤት

“ቤት” የሚለው ቃል በቤቱ ውስጥ የሚኖሩትን ቤተ ሰቦች የሚያመለክት ፈሊጣዊ አነጋገር ነው። አ.ት፡ “የአክዓብ ዘሮች”።

በምክራቸው ሄደሃል

በመንገድ ላይ መሄድ አንድ ሰው የሚኖረውን ሕይወቱን የሚያመለክት ዘይቤአዊ አነጋገር ነው። አ.ት፡ “ዖምሪና አክዓብ ሕዝቡ እንዲያደርጉ የነገሯቸውን አንተ ታደርጋለህ” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

የፈራረሰ ከተማ አደርግሃለሁ፣ እናንተን ነዋሪዎቿንም የመሳለቂያ ምልክት

ሚክያስ ሊሰማው ለማይቻለው ለከተማው ለራሱ የሚናገር ይመስል ሊሰሙት ለሚችሉት ለከተማይቱ ሰዎች ይናገራል። ዋና ቃል ገዳፊዎች የተውአቸውን ቅላት ግልጽ ማድረግ ይኖርብህ ይሆናል። አ.ት፡ “ከተማህን ፍርስራሽ አደርጋታለሁ፣ እናንተን ነዋሪዎቿንም የመሳለቂያ ምልክት አደርጋችኋለሁ” ወይም “የፈራረሰች ከተማ አደርግሃለሁ፣ የከተማይቱ ነዋሪዎች፣ የሚያዩህም ሁሉ እንዲሳለቁብህ አደርጋለሁ” ወይም “ከተማይቱን ፍርስራሽ አደርጋታለሁ፣ በነዋሪዎቿም ላይ ሰዎች እንዲሳለቁ አደርጋለሁ”።

የሕዝቤን ወቀሳ ትሸከማለህ

“ሕዝቤ ስለሚወቅስህ መከራን ታያለህ”